መነሻ ገጽ ሰበታ ከተማ የአሰልጣኞች አስተያየት | ስሁል ሽረ 1-0 ሰበታ ከተማ
ሰበታ ከተማስሁል ሽረዜናዎችየአሰልጣኞች አስተያየትየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የአሰልጣኞች አስተያየት | ስሁል ሽረ 1-0 ሰበታ ከተማ

አጋራ
አጋራ

ትግራይ ስታድየም ላይ ሰበታ ከተማን ያስተናገዱት ስሑል ሽረዎች ጨዋታውን በአሸናፊነት አጠናቀዋል።ከጨዋታው በኃላ የሁለቱ ክለብ አሰልጣኞች ሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል

አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ (ስሁል ሽረ)

“የዛሬ ጨዋታ እንዳያቹሁት በጣም ጠንካራ ፋክክር የታየበት ነው።እኛ ይሄ ነጥብ እጅጉ ያስፈልገን ነበር።ይሄን ሥስት ነጥብ ማሳካት ከቻልን የቡድናችንን ደረጃ እንዲሁም በራስ መተማመን በከፍተኛ ሁኔታ ሚያስተካክል ስለነበረ ተጨዋቾቹ ሁለቱ 45 ላይ የተሰጣቸውን ታክቲክ በአግባቡ ተወጥተው መውጣት ችለዋል ነገር ግን ከእረፍት በፊትም በኃላም ብዙ ያለቀላቸውን ኳሶችን ነው የሳትነው እና 1ለ0 ሳይሆን ከዛ በላይ አስቆጥረን ማሸነፍ ይገባን ነበር።እኛ የተጋጣሚያችንን የጨዋታ አቀራረብ ቀድመን አውቀነዋል በብዛት መሀል ሜዳ ላይ አጫጭር ኳሶች በመጫወት ሚመጡ ናቸው፤እራሳቸው ሜዳ ላይ ኳሱን በመልቀቅ ወደ ራሳችን ሜዳ ክፍል ላይ ሲገቡ የመከላከል ሁለተኛው ሜዳ ክፍል ላይ ተጭነን ኳሱን በመንጠቅ በመልሶ ማጥቃት የምንፈልገውን ነገር ማሳካት ችለናል።ተጨዋቾቹ ዛሬ ላሳዩት መስዋዕትነት ሊመሰገኑ ይገባል።”

አሰልጣኝ ዉበቱ አባተ (ሰበታ ከተማ)

“ጨዋታው እንዳያቹሁት ክፍት ነበር።በርካታ ጎሎች ሊቆጠሩ ይችሉ ነበር በሁለታችን በኩል፤አጨቃጫቂ ፍፁም ቅጣት ምት ቢሆንም በዛ አስቆጥረው ማሸነፍ ችለዋል።ከዛ ይልቅ በነሱ በኩልም በርካታ ግብ ሊሆኑ ሚችሉ እድሎችን ስተዋል፣እኛም ብዙ እድሎችን ፈጥረናል።”

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...