የአሰልጣኞች አስተያየት
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ (ሰበታ ከተማ)
ስለ ጨዋታው
– እግር ኳስ ጨዋታ ዘጠና ደቂቃ ሲደመር ተጨማሪ ሰአት ነው:: ከእረፍት በፊት የተሻለ ነገር ነበረን ከእረፍት በኋላ ደግሞ ፋሲሎች በብዙ ነገር የተሻሉ ነበሩ ::
ከእረፍት በኋላ የተፈጠረው ብልጫ ሁለተኛው አጋማሽ በተጀመረ በመጀመርያዎቹ ሁለት ደቂቃዎች ላይ ያስቆጠሩት ሁለት ጎሎች የራስ መተማመናቸውን ከፍ አድርጎላቸዋል :: ይህ ደግሞ የእኛ የተከላካይ ክፍል መዘናጋት ነው :: ይህም ለረጅም ሰአት ወደ ጨዋታው ለመመለስ ተቸግረን ነበር ::
እኛ የሁለተኛው አጋማሽ የመጀመሪያው ደቂቃ የሰራነውን ስህተት ፋሲሎች በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ላይ ደግመውታል ::
በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ጎል አግብተን መውጣታችን ለእኛ ጥሩ ነገር ነው :: የተጫወትነው ጥሩ ስብስብ ካለው ቡድን ጋር ነው ::
ስለ ደጋፊው
– ጨዋታው ለእኛ ከሜዳ ውጪ ያደረግነው ነው ሊባል የሚችል ነው :: የነበረው ደጋፊ ሙሉ ለሙሉ የፋሲል ነበር ማለት ይቻላል : ለእኛ ጥሩ የሚባል ውጤት ነው ::
ይህ ቡድን ያሳደከው ነው ባሳደከው ቡድን የመቀጣት ያህል ስሜት አልተሰማክም ?
የትም ብትሆን ለእግር ኳሱ ነው የምትሰራው :: እኔ የሰራሁት ነገር አልፋል ::
ቢሆንም ከመጀመሪያው አሰላለፍ ከነበሩት አስራ አንድ ተጫዋቾች አስሩ የነበሩ ልጆች ናችው :: ነባር ቡድንን መግጠም ከባድ ነው እኔም ሰራሁት ሌላ ሰው ያንን ከባድ ነገር ነው ያየሁት እንጂ ለእኔ ያው ነው :: እዛም እዚም የሚጫወቱት ለአንድ ሀገር ነው ::
አሰልጣኝ ስዩም ከበደ (ፋሲል ከነማ)
ስለ ጨዋታው
የመጀመሪያው አጋማሽ እኔ እንደጠበኩት አይደለም ያንንም እረፍት ሰአት ላይ ብዙ ተነጋግረናል ያንንም ብዙ አርመናል ::
ሁለተኛው አጋማሽ አጀማመራችን በጣም ጥሩ ሆኖ ሳለ ከነበረብን መከላከል የተሻለ ነገር ለማድረግ ጥረናል ::
የባከነ አራት ደቂቃዎች እስኪጨመር 3 ለ 1 እየመራን ነበር :: ኳስ ጨዋታ ይህ ነው : ለብዙ የሚያስተምር ነው ለሀገራችን ክለቦች ብቻ ሳይሆን ለአለምም የሚተላለፍ ቢሆን ይህ አስተማሪ ነገር ነው ::
ጨዋታ ማለት ዘጠና ደቂቃ እስከ አልጨረስከው ድረስ ትርጉም የለውም :: በተለይ የመጨረሻዎቹ ሶስት እና አራት ደቂቃዎች ተጫዋቾቼ ጨርሰናል ብለው በውስጣቸው ደስታ የፈጠሩ ይመስለኛል :: ቦታዎችን ትተዋል ትኩረት ማነስ ነበር:: ከበረኛው ጀምሮ ቦታ አጠባበቃችን ጥሩ አልነበረም ::
ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላም ለተጨዋቾቼ የነገርኳቸው ትልቅ ትምህርት ሊሆነን እንደሚገባ እና በትልቅ ትኩረት ልንጫወት እንደሚገባ ነው ::
አስተያየት ይስጡ