መነሻ ገጽ መቐለ 70 እንደርታ የአሰልጣኞች አስተያየት | መቐለ 70 እንደርታ 1-0 ወልዋሎ አዲግራት ዮንቨርሲቲ
መቐለ 70 እንደርታሪፖርትወልዋሎየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የአሰልጣኞች አስተያየት | መቐለ 70 እንደርታ 1-0 ወልዋሎ አዲግራት ዮንቨርሲቲ

አጋራ
አጋራ

የአሰልጣኞች አስተያየት 

አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ (መቐለ 70 እንደርታ)

“ጨዋታው የደርቢ ስሜት ስለነበረው ከበድ ያለ እና ውጥረት የበዛበት ነበር፤ነገር ግን ሁሉም ነገሮች ተቆጣጥረን ለመውጣት ብዙ ጥረት አድርገናል።ጨዋታው ላይ እንደነበረን ብልጫ እና በላይነት አንድ ለ ዜሮ ሊጠናቀቅ አይገባውም ነበር የሚል እምነት አለኝ።ሆኖም ዋናው ነገር ማሽነፍ ስለነበር አሸንፈን ስለወጣን ደስተኞች ነን።በአጠቃላይ ጨዋታውም በሰላም መጠናቀቁ ጥሩነው።”

ስለ ስፖርታዊ ጨዋነት

የሰላም ጉዳይ ላይ የኛ ክልል እሚታማ አይደለም።በአሁኑ ሰዓት በሌሎች ክልልም ተመሳሳይ ነገር እየታየ ስለሆነ የአሁኑም የዚህ ነፀብራቅ ናቸው ብዬ ነው ምገምተው።ከዚህ ውጪ አልፎ አልፎ ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጪ እሚታዩ ስድቦች መጥፋት አለባቸው።ሌሎች ክልሎች አማራ፣ሲዳማ ሄደን ጥሩ አቀባበል ነው የተደረገልን እና ጥሩ ነገር እያየን ስለሆነ መቀጠል አለበት እላለው።

አሰልጣኝ  ዮሐንስ ሳህሌ (ወልዋሎ አዲግራት ዮንቨርሲቲ)

“የተሻሉ ነበሩ አሸንፈዉናል፤በተለይ የመጀመርያ አጋማሽ ላይ የኛ ልጆች አፈግፍገው ነበር። ምንም የሰራነው ነገር የለም።በዛችም ስህተት ምክንያት ጎል አግብተው አሸንፈውናል።ከእረፍት በኃላ የተሻለ ነገር ለማድረግ ሞክረናል ወደ ጎል ብዙ ሄደናል ነገር ግን የተሻሉ እነሱ ነበሩ ከመጀመርያው፣በጭንቅላት ዝግጅት በልጠውናል በዛ ምክንያት አሸንፈውናል።

ያለፋት ሁለት ጨዋታዎች ላይ አለማሸነፋቸውን በተመለከተ

“የጅማ ጨዋታ የታክቲክ አካሄዳችንን አጥንተው ስለመጡ ለማሸነፍ ሳይሆን በተቻለ መጠን ከሜዳ ውጪ ነው በማለት እኩል ወጥተው ለመሄድ ስለሆነ ነበር ያሰቡት በዛ ምክንያት የፈለጉትን አንድ ነጥብ ይዘው ሄደዋል።የዛሬው ግን ተበልጠን እንጂ ሌላ ነገር አይደለም።ከእረፍት በፊት እነሱ በብዛት ወደ ጎል እንኳን ባይሄዱ ኳሱን በመያዝ የኛ ደግሞ ኳስ በማሳደድ ዉጤታማም ባይሆን ከግቡ ውጭ፤ግቡ የበረኛ ስህተት ነው የገባብን ለአማኑኤል ትልቅ ክሬዲት እሰጠዋለው መትቶ ነው ያገባው  ጎል ነው፣ በረኛችን ግን በሱ ስህተት ነው የገባብን።በአጠቃላይ በዛሬው ጨዋታ መቐለ ከእኛ የተሻለ የመጫወትና የማሸነፍም ፍላጎት ስለነበራቸው በማንም ማሳበብ አንፈልገም ተሸንፈናል።

ስለ ስፖርታዊ ጨዋነት

“አንዳንድ ስህተቶች አሉ መኖር ማይገባቸው ናቸው፣ በየትኛውም ወገን ተቀባይነት የሌላቸው ናቸው።ይሄ ኳስ ነው መዝናኛ ነው ሌላ ቦታ አይደለም፣እኔ ጋ መቐለ የነበሩት ወልዋሎ ይሄዳሉ፣ወልዋሎ የነበሩትም መቐለ ይሄዳሉ በዛ ደረጃ ኳሱ ላይ ብናተኩር ሌላው ነገር ቢቀር።ህፃናቶች፣ሽማግሌዎች ይገባሉ ምንናገራቸው ቃላቶች ለነኛ አካባቢያችን ላሉ ሰዎች በየትኛውም ወገን አይመጥኑም ስለዚህ እነዚህ ነጋሮች ቢሻሻሉ ጥሩ ይመስለኛል።ከዛህ ውጪ የከበደ ነገር አላየሁም ከስድቦቹ በስተቀር።”

የአብዱላዚዝ ኬይታ ቀይ ካርድ በተመለከተ

ቀይ ማግኘት አለበት የለበትም ይሄ ከዳኛው ጋራ በነሱ በህጋቸው መሄድ የሚገባው ነው ግን ቀዋሚ በረኛህን ማጣት ማለት ሌላ ታስገባለህ ግን ማጣት አይገባህም ጨዋታው ካላቀ በኃላ በሚደረጉ ሜዳ ላይ ባልተደረጉ ነገሮች በተለይ ተጨዋችህን ስጣታ፣ምንም ቢሆን የፈለገ ነገር ቢሆን የበረኛችን ስህተት ነው።ምንም በተባባሉ ባላቅ ቀይ እስከሰጠው ጊዜ ድረስ፣ ጨዋታው አልቋል ጨዋታ ካለቀ ሌላ ነገር ምን ያስፈልጋል ስለዚህ ሙሉ ለሙሉ እምፈርደው በበረኛው ላይ ነው።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ፉአድ ኢብራሂም (ኢትዮጵያ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...