የአሰልጣኞች አስተያየት || ሀዋሳ ከተማ 1-1 ሀዲያ ሆሳዕና

 

ሁለተኛ ሽንፈት ላለማስተናገድ በጥንቃቄ ነው የተጫወትነው” አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማሪያም – ሀዲያ ሆሳእና 

ጨዋታው ሁለት መልክ ነበረው በኳስ ቁጥጥሩ ሁለታችንም ተመጣጣኝ ነበርን አልፎ አልፎ በመልሶ ማጥቃቱም ተመሳሳይ ባህሪ ነበረን።ሁለተኛ ሽንፈት ላለማስተናገድ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርገን ነው የተጫወት ነው።እየተወዳደርን ቡድን እሰራን ነው ያለ ነው።ያሉንን ክፍተቶች ለመሞላት ወደ ቡድኑ የቀላቀል ናቸው አራት ተጫዋቾች ለመጠቀም ሞክረናል በመጀመሪያ ዙር እና በሁለተኛ ዙር ልጆቹን ብናምጣም ከዝግጅት አንፃር ሁለት ሶስት ቀን ነው ከቡድኑ ጋር የቆዩት አሁንም ቢሆን ከቡድናችን ጋር የመዋሀድ እና የቅንጅት ችግር አለባቸው።ባሉን ሀያ ያክል የእረፍት ቀን ባካል ብቃት ያልተስተካከሉ ልጆች አሉ ይህን ለማስተካከል ጠንክረን እንሰራለ።

“ልጆቹ ላይ ምን ችግር እንዳለ አላውቅም”
የሀዋሳ ከተማ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ብርሀኑ ወርቁ ሀዋሳ ከተማ

ጨዋታውን እንደጠበኩት አላገኘውትም ሜዳችን ላይ ማሸነፍ አቅሙ ነበረን ዛሬ ትንሽ ተቀዛቅዘን ነው የተገኘነው።ልጆቹ ላይ ምን ችግር እንዳለ አላውቅም ሜዳ ከመግባታቸው በፊት የሚያሳዮት ነገር ጥሩ ነበር ሜዳ ውስጥ ግን ፊት ያላቸውን ነገር አውጥተው እየተጫወቱ አልነበረም።አቤኔዘር ከገባ በኳላ አጨዋወታችን ወደ ኳላ ነበርቲማችን አብዛኛው ተጫዋች ተዳክሞ ነበር ውጪ ላይ ካሉ የተሻሉ የምንለው እነዚህን ስለነበረ ለመጠቀም ሞክረናል።