ሀትሪክ ትኩረት | የአሰልጣኞች ስንብት እና ድህረ ጨዋታ አስተያየቶች

👉👉 እኔ ስለ ዳኛ ምንም ማለት አልፈልግም ማውራት ምፈልገው ስለ እራሴ እና ስለቡድኔ ነው። ጳውሎስ ጌታቸው (ጅማ አባ ጅፋር)

👉👉አንድ ዳኛ ዳኛ እስከሆነ ድረስ በእኩል አይን ማጫወት አለበት። (አስቻለው ኃ/ሚካኤል የአዳማ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ)

👉👉ህዝቡም ያየው ነገር ስለሆነ ህዝብ ይመልሰው ዳኛው እራሱ ይፍረደው። (ዘርዓይ ሙሉ ሲዳማ ቡና)

👉👉ሁለተኛ ስትራቴጂ የሚባለው ነገር የተጫዋች ለውጥ ያስፈልጋል። (ካሳዩ አራጌ ኢትዮጵያ ቡና)

 

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 13ኛ ሰምንት ትላንት ፍፃሚያቸውን አድርገዋል። በውጤት እና በተለያዩ ምክንያቶች ክለቦች ከአሰልጣኞቻቸው ጋር በመለያየት ነው የሚገኙት። በተጨማሪም አሰልጣኞች እየሰጡ የሚገኙት አስተያየትም ቀልብ ሳቢ ሆኗል።

የአሰልጣኞች ስንብት

በዚህ አመት በጠቅላላ 3 ቡድኖች በውጤት ቀውስ ምክንያት ከአሰልጣኞቻቸው ጋር ሲለያዩ ዮሐንስ ሳህሌ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ የመለያየታቸው ነገር እርግጥ ሆኗል። የወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ ቦርድም የአሰልጣኙን የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ተቀብሏል። በዚህ መሰረትም አስልጣኙ ከዚህ በኋላ ቡድኑን እንደማይመሩ ታውቋል። በዚህ ሳምንት ግርማ ታደሰ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር የተለያየ ሌላኛው አሰልጣኝ ሆኗል። አሰልጣኞቻቸው ካሰናበቱ ክለቦች መካከል ሀድያ ሆሳዕና ብቻ ፀጋየ ኪዳነማርያምን ዋና አሰልጣኝ አድርገው መቅጠር ሲችሉ ሌሎቹ በረዳት አሰልጣኞቻቸው እየተመሩ ነው።

በዚህ ሳምንት ከተሰጡ አስተያየቶች በዳኝነት ችግር ምክንያት አሰልጣኞች በምሬት ሲናገሩ ተደምጠዋል።

ጳውሎስ ጌታቸው (ጅማ አባ ጅፋር)

መጀመሪያ ሀዋሳዎችን እንኳን ድስ ያላቹህ ለማለት እወዳለው። በመቀጠል ጨዋታው እንዳያችሁት ሳቢ ነበር። እዚያም እዛም ሲሞከር ነበር ብዙ ነገር አይታችኋል። የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ቀይ ካርድም ነበር ጨዋታውን በሙሉ በጎዶሎ ተጨዋቾች ነው የጨረስነው በመልሶ ማጥቃት ነበር የተጫውትነው። እኔ ስለ ዳኛ ምንም ማለት አልፈልግም ማውራት ምፈልገው ስለ እራሴ እና ስለቡድኔ ነው። ሙሉ 90ደቂቃ የሚችሉትን ሁሉ አርገዋል የመጨረሻውንም ሰዓት እንደዚህ ነው ምለው ነገር የለም። ፍርዱን ለእናንተው ትቻለሁ ባጠቃላይ ግን የጨዋታው እንቅስቃሴ ለኔ ጥሩ ነበር። ግን ያው ጨዋታ እንዳያምር የሚያደርጉትም ዳኞች ናቸው እንዲያምር ሚያደርጉትም ዳኞች ናቸው ባጠቃላይ ጥሩ እንቅስቃሴ ነበር።

ስለ ተጨዋቾች ስሜታዊ መሆን

እናንተ የተመለከታቹት የተጨዋቾችን ሰህተት ነው ተጨዋቾቹ ገና ወጣቶች ናቸው ቶሎ ስሜታዊ ይሆናሉ። መጀመሪያ እናንተ መቅረፍ ያለባቹ ሜዳ ላይ ያለውን ሰተት ነው የሜዳው ስተት ከተቀረፈ ሁሉም ነገር በትክክል የተጫወት ያሸንፍ። ለኢትዮጵያ ኳስ እድገትም ሚበጀው እንዲህ ቢሆን ነው።

ዘርዓይ ሙሉ ሲዳማ ቡና

ስለ ዳኝነት

እሱን ለዳኛው ትቸዋለው። ህዝቡም ያየው ነገር ስለሆነ። ህዝብ ይመልሰው። ዳኛው እራሱ ይፍረደው።

(አስቻለው ኃ/ሚካኤል የአዳማ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ)

ጨዋታው እንዳያችሁት ጥሩ ጨዋታ ነበር የተካሄደው በሁለታችን በኩል። ግን አስምሬ መናገር የምፈልገው ባለፈውም ተናግሪያለው ዳኞች ከሜዳ ውጭ ለሚጫወተው ቡድን ተፅእኖ እያሳደሩ ነው። ፌደሬሽኑም እዚ ላይ መስራት አለበት። አንድ ዳኛ ዳኛ እስከሆነ ድረስ በእኩል አይን ማጫወት አለበት። ጥሩ ኢንተርናሽናል ዳኞች አሉ ውጭ ሳይቀር ሄደው የሚያጫውቱ ከነሱ ልምድ መውሰድ ይኖርባቸዋል። ዋና ዳኛው ጥሩ ነበር ረዳቶቹ ግን ምንም አላገዙትም። ፌደሬሽኑ ያስብበት እውነተኛ ዳኝነት እንፈልጋለን። ሁለታችንም ጥሩ ኳስ ነው የተጫወትነው ያገኘናቸው ኳሶች ባለመጠቀማችን ግን ዋጋ አስከፍለውናል። ተጫዋቾቻችን ስሜታዊ ያደረጉት ዳኞች ናቸው። በመጨረሻ የዳኝነቱ ነገር በደምብ ይታሰብበት።

ብቸኛው የዚህ ሳምንት የካሳየ አራጌ አስተያየት ስለ አጨዋወታቸው እና ጫናዎቻቸው የተናገሩት አነጋጋሪው አስተያየታቸው ነው።

ካሳዩ አራጌ (ኢትዮጵያ ቡና)

“ጨዋታው በአጠቃላይ ጥሩ ነው። በአጠቃላይ የምለው ነገር ሂደቱን መታገስ ይገባል። በየሰከንዱ ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል መድረስ አይቻልም። መድረስ ይቻላል ግን አስተማማኝ አይደለም። ይሄ ነው ተጫዋቾች ላይ ጫና የፈጠረው። ተጫዋቾቹ በነፃነት እንዲጫወቱ ማድረግ አለብን። ከውጤት መራራቅ ስላለ በሁለተኛው አጋማሽ መጣደፍ ውስጥ ገብተዋል። የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ተጭነን ተጫውተናል። በሁለተኛው አጋማሽ የኛ ሜዳ ላይ ተጭነው ተጫውተዋል። በዚህ አይነት መንገድ ሲመጣ ለመውጣት ይቸግራል። በዛ ሰዓት በሚኖሩ ሂደቶች የሚበላሹ ኳሶች ይኖራሉ።”

ቡና ሁለተኛ ስትራቴጂ አያስፈልገውም ?

“ሁለተኛ ስትራቴጂ የሚባለው ነገር የተጫዋች ለውጥ ያስፈልጋል። ስትራቴጂ መቀየር ካስፈለገ ኳስ ተጫዋች መለወጥ ያስፈልጋል።”

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor