የአሰልጣኞችን ውል በማደስ ለ2013 ውድድር አመት ዝግጅቱን የጀመረው ድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ክለብ የመጀመሪያ ተጫዋች አስፈርሟል።

 

ድሬድዋ ከተማ የአማካይ ተከላካይ የሆነውን አስጨናቂ ሉቃስ በአንድ አመት ኮንትራት ማስፈረም ችሏል። የሐዋሳ ከነማ ኮንትራቱን ዘንድሮ የጨረሰው አስጨናቂ ከዚህ በፊት ለደቡብ ፖሊስ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተጫውቶ ማሳለፉ ይታወሳል ።


ድሬዳዋ ከተማ በመፈረሜ ደስ ብሎኛል ያለው አስጨናቂ ” የፍቅር ከተማ ከሆነች ድሬ ጋር ጥሩ ነገር ለመስራት ነው አላማዬ” ብሏል ። በሚቀጥለው አመት ጥሩ የፕሪሚየር ሊግ ተፎካካሪ ለመሆን ያለመው ድሬድዋ ከተማ በሚቀጥሉት ጊዜያትም አዳዲስ ተጫዋቾችን ያስፈርማል ተብሎ ይጠበቃል ።

ድሬድዋ ከተማ የዘንድሮው የውድድር ዓመት በኮሮና ቫይረስ እስከ ተቋረጠበት ድረስ ሊጉን በአስራ ሰባት ጨዋታዎች ሀያ አንድ ነጥቦችን ሰብሰቦ ከወራጅ ቀጠናው በሁለት ነጥቦች ብቻ ርቀው ተቀምጠው ነበር ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor