የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ በቅርቡ በሞት ያጣነው ታላቁ የእግር ኳስ ባለሙያ አሰልጣኝ ስዩም አባተ የ40 ቀን መታሰቢያ ዛሬ ታስቦ የሚውል ሲሆን ለምርጡ የሀገር ባለውለተኛ የተዘጋጀው የመታሰቢያ እግር ኳስ ውድድርም እሁድ ዕለት በቄራ አልማዝዬ ሜዳ ላይ ፍፃሜውን ያደርጋል።
የእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመኑ ላይ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ከታዳጊ ቡድን አንስቶ እስከ ዋናው ቡድን ድረስ እንደዚሁም ደግሞ ለትግል ፍሬ ለሸዋ ምርጥ ለመሂሰማ እና ለብሄራዊ ቡድናችን በጥሩ ብቃቱ እና መልካም ባህሪው ለተጫወተው በመቀጠል ደግሞ በአሰልጣኝነት የህይወቱ ዘመኑ የቆርኪና ጣሳ የኒያላ የህዝብ ማመላለሻ የኢትዮጵያ ቡና የመድን የባንክ የሰሚት የአየር መንገድ የብርሃንና ሰላም እና ብሄራዊ ቡድኖቻችንን ከታዳጊው አንስቶ እስከዋናው በማሰልጠን ላለፈው እና በአሰለጣጠን እና በተጨዋቾች የአመላመል ብቃቱም የብዙዎቹን ቀልብ ለመግዛት የቻለውን እንደዚሁም ደግሞ በቴክኒካል ዳይሪክተርነትም በቡና ኒያላ ቄራ አንበሳ እና በብሄራዊ ቡድን ውስጥም በመስራት ጥሩ ግልጋሎት ሰጥቶ ያለፈውን አሰልጣኝ ስዩም አባተን ለማሰብ የተዘጋጀው የ6ቱ የከፍተኛ ሊግ ክለቦች ውድድር ነገ ፍፃሜውን ሲያደርግ ለዋንጫ በማለፍ ወሳኙን ጨዋታ የሚያደርጉት ናኖ ሁርቦን በፍፁም ቅጣት ምት ያሸነፈው የንፋስ ስልክ ላፍቶ እግር ኳስ ቡድን እና ቄራ አንበሳነት ያሸነፈው የልደታ እግር ኳስ ቡድን ነው።
እሁድ የሚደረገው ሌላኛው የፍፃሜ ጨዋታ ደግሞ ባለፈው ሳምንት ተደርጎ በነበረው የመክፈቻ ጨዋታ ላይ 1ለ1 በሆነ ውጤት የተለያዩት የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና ተጨዋቾች ከቄራ አንበሳ የጤና ቡድን ጋር የሚያደርጉት ፍልሚያ ሲሆን ለአጠቃላይ ውጤት አሸናፊው ቡድንም ዋንጫ የሚሰጥ ይሆናል።
የአሰልጣኝ ስዩም አባተ
ይኸው የመታሰቢያ ጨዋታ ነገ ፍፃሜውን ሲያደርግም ውድድሩን ያዘጋጀው የቄራ አንበሳ ስፖርት ክለብ የስፖርት አፍቃሪው በአልማዝዬ ሜዳ ተገኝቶለት ውድድሩን እንዲመለከትለት ጋብዟል።
አስተያየት ይስጡ