በሞት ላጣነው የሀገር ባለውለተኛው አሰልጣኝ ስዩም አባተ የተዘጋጀው የመታሰቢያ ዋንጫ ነገ ይጀመራል
የኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ ውስጥ በተጨዋችነትም በአሰልጣኝነትም በሙያቸው ትልቅ ግልጋሎትን ለሀገርም ለበርካታ ክለቦችም ሰጥተው ያለፉትን ታላቁን የስፖርት አባት እና በቅርቡ በሞት ያጣናቸውን አሰልጣኝ ስዩም አባተን ለማስታወስ እና ለመዘከር በ 6 የከፍተኛ ሊግ ክለቦች መካከል በስማቸው የተዘጋጀ የመታሰቢያ ውድድር የሚደረግ ሲሆን ይህም ጨዋታ ከነገ ጠዋት አንስቶ በቄራ አልማዝዬ ሜዳ ላይ ይካሄዳል።
በአሰልጣኝነት የህይወት ዘመናቸው በክለብ ደረጃ ኢትዮጵያ ቡናን እና በርካታ ክለቦችን እንደዚሁም ደግሞ የብሄራዊ ቡድናችንን በማሰልጠን በሚሰሩት ጥሩ ቡድን በብዙዎች ዘንድ የሚደነቁት እና በተጨዋችነት ዘመናቸውም ለቅዱስ ጊዮርጊስ በመጫወት ከፍተኛ እውቅናን ያገኙት እኚሁ ባለሙያን ለማሰብ ነገ በሚደረገው የመክፈቻ ጨዋታ በቅድሚያ የሚጫወቱት ቡድኖች የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና ተጨዋቾች ከቄራ አንበሳ የጤና ቡድን ሲሆን በመቀጠል የሚደረገው ጨዋታ ደግሞ በ 6 የብሄራዊ ሊግ ክለቦች መካከል የሚደረገው ነው።
የአሰልጣኝ ስዩም አባተ መታሰቢያ የእግር ኳስ ውድድር ሙሉ ፕሮግራም የሚከተለው ሲሆን ጨዋታዎቹን የስፖርት አፍቃሪዎች ከነገ አንስቶ በቄራ አልማዝዬ ሜዳ እንዲከታተሉም በአዘጋጁ አካል ተጋብዘዋል።

አስተያየት ይስጡ