የአርቢትሮቹ የዝግ ውይይት በሠላም ተጠናቀቀ

 

በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚገኘው መሠብሠቢያ አዳራሽ አርቢትሮቹና ኮሚሽነሮቹ በተሠበሠቡበት መድረክ ፕሬዝዳንቱ አቶ ኢሳያስ ጅራና የሊግ ኮሚቴው ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ተገኝተው ማስገንዘቢያና ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡ በዝግ የተካሄደው ስብሰባ ሲከፈት በጎ ውሳኔዎችን ወስኖና ተስማምቶ ጨርሷል፡፡

በ2ኛ ዙር 120 ጨዋታዎች ላይ የዳኞች ኮታ ወይም ማዳረስ አይኖርም የብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ አሁን ወደ ጥራትና ጨዋታውን ማን በሰላም ያጠናቅቀዋል ብለን ያመንባቸውን ዳኞች የትኛው ኮሚሽነር ነው ጨዋታውንና አርቢትሮቹን ገምግሞ ተገቢ ሪፖርት የሚያቀርበው ብለን ምደባ ስለምናደርግ ተደጋጋሚ ፊቶችን ልናይ እንችላለን ሲሉ ብቸኛ መመዘኛ ብቃት ብቻ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ ጊዜው ወሳኝ በመሆኑ የተሻሉትን ለመምረጥ እንሞክራለን በዚህ በኩል ቅሬታዎችን አንቀበልም በማለት አስረድተዋል፡፡

ሁለቱ አመራሮች ደግሞ ጊዜው ምርጫ የተቃረበበት እንደመሆኑ ስታዲየሞች ውስጥ ምንም አይነት ፖለቲካዊ አጀንዳዎች ማስተናገድ የለባችሁም…የየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አርማዎች ፖለቲካዊ መልዕክት የሚያስተላልፍ ምንም አይነት ነገር ካያችሁ ጣልቃ ሳትግቡ ግን ግልጽ ያለ ሪፖርት አምጡ ሊግ ኮሚቴው ርምጃ ይወስዳል ኳሱን ከፖለቲካ መንደርነት ልናድነው ይገባል ይሄ የጋራ ሃላፊነታችን ነው በማለት በሁሉም ወገኖች ስምምነት ተጠናቋል፡፡

አርቢትሮች ከ11ኛ ሳምንት ጀምሮ ክፍያቸው እንደቆመና ችግር እንደተፈጠረ ሊግ ኮሚቴው የቀረበለት ነገር የለም ለዚህም እናዝናለን ነገር ግን የ2ኛ ዙር ክፍያ በወቅቱ እንዲደርሳችሁ እናደርጋለን በ1ኛ ዙር እንዲጨመር የተወሰነው በነፍስ ወከፍ 2ሺህ ብር የሙያ አበላችሁ በቀናት ውስጥ እንዲከፈል እናደርጋለን በማለት ዳኞኝን ባስደሰተ መልኩ ተፈጽሟል፡፡

ሊግ ኮሚቴና ፌዴሬሽኑ በጋራ እንደድርሻቸው ከሰሩ ጥሩ ነገር ልናይ እንደምንችል የአቶ ኢሳያስና የመቶ አለቃ ፈቃደ
የስራ ሂደት ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport