By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: “የትግራይ ሕዝብ ለምን ይቅርታ ይጠይቀኛል? ኳስ የማያውቅ ሰው በፈጠረው ችግር ሕዝቡ ይቅርታ መጠየቅ አይጠበቅበትም”ፌዴራል አርቢትር እያሱ ፈንቴ
Share
Notification Show More
Latest News
በጨምበላላ ዋዜማ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጣፋጭ ድል ቀምሷል
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የጨዋታ ዘገባ
ዩጋንዳዊው የሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ በዛሬው ጨዋታ አይሰለፍም
ሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች
የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ አመራሮች ከሀላፊነት ለመነሳት ፍቃደኛ ሆኑ
ዜናዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ
የሲዳማ ቡናው ግብ ጠባቂ ታገደ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች ሲዳማ ቡና
መቐለ 70 እንደርታ ናይጄሪያዊ አጥቂ አስፈረመ
የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች መቐለ 70 እንደርታ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ወልዋሎየትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበርየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

“የትግራይ ሕዝብ ለምን ይቅርታ ይጠይቀኛል? ኳስ የማያውቅ ሰው በፈጠረው ችግር ሕዝቡ ይቅርታ መጠየቅ አይጠበቅበትም”ፌዴራል አርቢትር እያሱ ፈንቴ

ዮሴፍ ከፈለኝ
ዮሴፍ ከፈለኝ 8 years ago
Share
SHARE

በዮሴፍ ከፈለኝ

​የሰሞኑ ትልቁ መነጋጋሪያ ማነው ከተባለ 

አርቢትር ኢያሱ ፈንቴ ቅድሚያውን ይወስዳል፡

፡ በወልዋሎ ቡድን መሪ ማሩ ገ/ፃዲቅ ከተደበደበ 

- ማሰታውቂያ -

በኋላ የሁለቱ ምስል በውጪም በሀገር ውስጥም 

ኳስ በሚወዱም ሆነ ደንታ በማይሰጠው 

የህብረተሰብ ክፍል ትኩረት የሳበ ክስተት ሆኖ 

አልፏል፡፡ ባለፈው ሀሙስ ከመቀሌ ኤፍ ኤም 

ጋዜጠኛ ነኝ ካለው ጋዜጠኛ ዮናስ ጋር ቆይታ 

ያደረገው ኢያሱ አነጋጋሪ ምላሽ ሰጥቷል፡፡ 

ሁሉም ሲሮጡ ሊደበድቡኝ ነው ብለህ 

ታምናለህ የተባለው ኢያሱ የሮጡት ታዲያ 

ሊስሙኝ ነው? ማሩ ያልቻለው ተጨዋቾቹ 

ስሜታቸውን ተቆጣጥረው ዝም ሊሉኝ ነው 

ሲል ያልተጠበቀ ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ከምትሮጥ 

ቀይ ካርድ አትመዝም ወይ ሲባል በዚያ ከበባ 

ውስጥ ካርድ ዋጋ አለው? እኔ ደግሞ ቆሜ 

መደብደብ አልሻም እንደ ወልዲያው ልጅ 

እንዲገጥመኝ አልፈልግም፡፡ ሰርቼ የምበላ ሰው 

ነኝ ማንንም ሰው አሳክሙኝ የምለው የለም 

ልጁ ገና እየተለመነለት ነው ሲል የተሰማውን 

ተንፍሷል፡፡ የሀትሪኩ ዮሴፍ ከፈለኝ አርቢትሩ 

እንዴት ዳግም ተናገረ? የተናገረውስ በርግጥ 

አርቢትር ኢያሱ ፈንቴ ነው? ለሚለው ጥያቄ 

ምላሽ ለማግኘት ከአርቢትሩ ጋር ያደረገው 

ቆይታ ይህን ይመስላል፡፡

 

ሀትሪክ፡- ለትግራይ ኤፍ ኤም ጣቢያ 

የሰጠኸው ቃለ ምልልስ አለ?

ኢያሱ፡- አንድ ልጅ ደውሎ ጠይቆኝ 

መልሻለው ጋዜጠኛ ግን አይደለም፡፡ የሆነ ወሬ 

አውርቶኛል፡፡

ሀትሪክ፡- የውይይታችሁ አንኳር ምን 

ነበር?

ኢያሱ፡- የትግራይ ህዝብ ይቅርታ 

ሊጠይቅህ ይፈልጋል አለኝ፡፡ 

ሀትሪክ፡- በርግጥስ ህዝቡ ይቅርታ መጠየቅ 

ነበረበት?

ኢያሱ፡- የለበትም የትግራይ ሕዝብ ለምን 

ይቅርታ ይጠይቀኛል? ኳስ የማያውቅ ሰው 

በፈጠረው ችግር ሕዝቡ ይቅርታ መጠየቅ 

አይጠበቅበትም፡፡ እኔ ደግሞ ከትግራይ ሕዝብ 

ጋር ፀብ የለኝም፡፡ ህዝቡ ደግሞ ምንም 

አላደረገኝም አልኩት፡፡ 

ሀትሪክ፡- ስለ ወልዋሎ ያወራኸው ነገር 

አለ?

ኢያሱ፡- አዎ! ምንም አይነት ችግር 

በሌለበት ወቅት ወልዋሎ ላይ ሪጎሬ ሰጥቼ 

ምንም አልተባልኩም፡፡ አሁን ምን ተገኘ? 

ወልዋሎ ሪጎሬ ተሰጥቶበትም አዲስ አበባን 

አሸንፎ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ አለፈ ዛሬ ምን 

ለወጣቸው ብዬዋለው፡፡ 

ሀትሪክ፡- ዳኛ ግን ለሚዲያ ማውራት 

ይችላል?

ኢያሱ፡- ስለጨዋታውኮ አላወራውም፡

፡ የተበደልኩት እኔ ነኝ፡፡ ስለተጎዳው ስሜቴ 

ባወራ ተገቢኮ ነው፡፡ ልጁ ጋዜጠኛ ነኝ 

አላለኝም፤ ለአካባቢው ህብረተሰብ ስለምቀርብ 

ነው የማወራህ ብሎኛል፡፡ 

ሀትሪክ፡- ወደ ዳኝነት የመመለስ እድሉና 

ፍላጎቱ አለህ?

ኢያሱ፡- እስካሁን አልተመደብኩም 

እነርሱም አልመደቡኝም እኔም አልፈለኩም፡፡ 

የፍርድ ቤት ጉዳይ ስላለኝ እርሱን መጨረስ 

እፈልጋለው ጠቅላላ የጤና ምርመራ ማድረግ 

አለብኝ፡፡ ፌዴሬሽኑ የወልዋሎን መጨረሻ 

ማየትና ከዚያ በኋላ የራስህ ጉዳይ ሊለኝ ነው 

የሚፈልገው፡፡ ይህን ጉዳይ አስቀድሜ መጨረስ 

እፈልጋለው፡፡ ፌዴሬሽኑ ውድድሩ እንዲጀመር 

ነው የሚፈልገው እንጂ የኔን ጉዳይ ማስተካከል 

አይፈልግም፡፡ እያጫወትኩ ጉዳዩን መከታተል 

ብፈልግም በቅርቡ በሰጠሁት አስተያየት ደስተኛ 

የሆነ አይመስለኝም፡፡ ቀሪ ጊዜ አለኝ ለማጫወት 

አልጓጓም፡፡ 

ሀትሪክ፡- በቀጣይ የፌዴሬሽኑን የዳኛ 

ኮሚቴን የማናገር እቅድ የለህም?

ኢያሱ፡- ብዙም ማናገር አላሰብኩም በየ3 

ሳምንት ወይም 4 ሳምንት የዳኝነት ምድብ 

ስለሚደረስ እኔም በቅርቡ በማጫወቴ ብዙም 

አልጠብቅም ለማንኛውም አመሰግናለሁ፡፡ 

ሀትሪክ፡- ትክክለኛ ሪፖርት ግን ፅፈሃል?

ኢያሱ፡– ሪፖርቱ ተቀይሯል የሚል ወሬ 

ሰምቻለው አንድ ጋዜጠኛ መጀመሪያ የፃፈው 

ሪፖርት ይህ ነው ጫና ተደርጎበት የፃፈውም 

ሁለተኛው ሪፖርት ይሄ ነው ብሎ አንቧል 

አሉ፡፡ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ጉዳዩን ለማጣራት 

እኔን፣ 4ኛው ዳኛና ኮሚሽነሩን ሰኞ 9 ሰዓት 

ላይ ጠርቶናል፡፡ (ኢንተርቪው የተሰራው ቅዳሜ 

ማታ ላይ ነው)

ሀትሪክ፡- ሪፖርትህ ላይ ሁኔታውን 

የገለፅክበት መንገድ ምን ይመስላል?

ኢያሱ፡- ቆይ ላንብልህ… በ2ኛው አጋማሽ 

ጊዜ በ72ኛ ደቂቃ ላይ የስታዲየም ፓውዛ 

የጠፋ ሲሆን መብራቱ እስኪበራ ጨዋታው 

ለ16 ደቂቃ ያህል ተቋርጧል፡፡ መብራቱ ከመጣ 

በኋላና ጨዋታው ቀጥሎ በ84ኛ ደቂቃ ቁጥር 

27 የሆነው የመከላከያው ፍፁም ገ/ማርያም 

የመታት ኳስ የጎሉ የውስጥ መስመር ያለፈ 

ሲሆን እኔም ከቁጥር 2 ረዳት ጋር በመናበብ 

ወደ መሀል ሜዳ ባመለከትን ጊዜ የወልዋሎ 

ግብ ጠባቂ ኳሷን ይዞ የመሃል ዳኛ በሆንኩት 

ኢያሱ ፈንቴ ላይ ከሁሉም የቡድን ጓደኞች 

ጋር በመሰብሰብ ቁጥር 1 በረከት አማረ፣ 

ቁጥር 3 አለምነህ ግርማ፣ ቁጥር 5 አሳሪን 

አልማሀዲን፣ ቁጥር 9 ማናዬ ፋንቱ፣ ቁጥር 

21 በረከት ተሰማ፣ ቁጥር 24 አፈወርቅ ኃይሉ 

ተብለው የተዘረዘሩት ተጨዋቾች ከሜዳ ውጪ 

ለመደባደብ እያሯሯጡ ካስወጡኝ በኋላ ምክር 

መስጫው ላይ ከነበሩትና ተቀይሮ የወጣው 

ቁጥር 16 ዋለልኝ ገብሬ በቀጥታ ወደኔ 

በመምጣት ድብደባ ፈፅመውብኛል፡፡ የቡድን 

መሪው አቶ ማሩ ገ/ፃዲቅ ከተጠባባቂ መቀመጫ 

ተነስተው በመምጣት ድብደባ ፈፅመውብኛል፡፡ 

የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማርያም፣ 

ም/ል አልጣኝ ሃብቶም ኪሮስና የቡድኑ ወጌሻ 

ቢኒየም ተፈሪ እነዚህ ሁሉ የድብደባው አካል 

ነበሩ፡፡ ከድብደባው በኋላ ውደድሩን ለመምራት 

የጤና ችግር ስለገጠመኝ ቀሪውን 6 ደቂቃ 

ውድድሩን መምራት ባለመቻሌ ጨዋታው 

ሊቋረጥ ችሏል፡፡ በመጨረሻው የመከላከያው 

ቁጥር 10 ዳዊት እስጢፋኖስ ቁጥር 27 ፍፁም 

ገ/ማርያም እና የወልዋሎው ቁጥር 4 ተስፋዬ 

ደበበ እኔን ከድብደባ ለማትረፍ ብለው ለከፈሉት 

መስዋዕትነት ሊመሰገኑ ይገባል ብዬ ፃፍኩ፡፡ 

ነገር ግን የቡድኑ አሰልጣኝ ም/ል አሰልጣኘና 

ወጌሻው አልተቀጡም፡፡ እንደማውቀው ሁለቱ 

ረዳቶች፣ ኮሚሽነሩ፣ አራተኛው ዳኛና እኔ 

በጋራ 5 ደብዳቤ ፅፈናል ምናልባት 4ኛው ዳኛ 

ጋር ይቀየር አይቀየር የማውቀው ነገር የለም፡

፡ ሁላችንም ፅፈን ለኮሚሽነሩ ይድነቃቸው 

(ቦቸራ) ነው የሰጠነው፡፡ የኔ ሪፖርት በራሴ 

ማህተም የተረጋገጠ ነው፡፡ በሁለት ኮፒ 

ስላሰራሁ ፌዴሬሽን ያለውና የያዝኩትን 

ማስተያየቴ አይቀርም፡፡ 4ኛ ዳኛው ብቻ ነው 

በእስክሪብቶ የፃፈው፡፡

 

ሀትሪክ፡- በቀጣይ ምን ለማድረግ አሰብክ?

ኢያሱ፡- ፊፋ በተደጋጋሚ ኮርስ ጥቶኝ 

ወስጃለው፡፡ ዌብሳይታቸውን ስለማውቅ 

ከቪዲዮ ጋር አያይዤ የተቀጡትና ይግባኝ 

ሰሚ የወሰነውን ጨምሬ ምናልባት ውሳኔው 

ተገቢ አይደለም ብዬ ካመንኩ ለፊፋ ለመላክ 

ተዘጋጅቼያለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- የተጨዋቾቹ ቅጣት ቢቀነስ 

ወይም ቢነሳላቸው…. ያንተ ምላሽ ምን 

ይሆናል? 

ኢያሱ፡- በጣም ይገርመኛል በጣም ነው 

የምስቀው ይህን ካደረጉ በቀጣይ የሚሆነውን 

አብረን እናያለን፡፡

You Might Also Like

በጨምበላላ ዋዜማ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጣፋጭ ድል ቀምሷል

ዩጋንዳዊው የሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ በዛሬው ጨዋታ አይሰለፍም

የሲዳማ ቡናው ግብ ጠባቂ ታገደ

መቐለ 70 እንደርታ ናይጄሪያዊ አጥቂ አስፈረመ

ጋናዊው ተጫዋች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ለመድን ፈረመ

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By ዮሴፍ ከፈለኝ
Follow:
Editor at Hatricksport
Previous Article ሪፖርት | ጅማ አባጅፋር መሪነቱን ከተከታዩ በሁለት ነጥብ እርቆ እሚወጣበትን እድል አምክኗል።
Next Article የ2010 ኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ በቀጥታ/ LIVESCORE/ ይከታተሉ

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
Uncategorized

በኘሪሜየር ሊጉ ደደቢትና ወልዲያ ድል ቀንቷቸዋል

Mussie Girmay By Mussie Girmay 9 years ago
ዋሊያዎቹን ሊደግፉ ተዘጋጅተዋል?
ምንተስኖት አሎ ስሑል ሽረን ተቀላቅሏል
ሪፖርት | ኢትዮጵያ ቡና በማሸነፍ ደረጃውን ማሻሻል ችሏል።
​የወልዲያ ስታዲየም የመግቢያ ዋጋ ላይ ማስተካከያ አደረገ 
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?