የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ሊከፈት ቀናቶች ቀርተውታል

 

የ2012 የኢትዮጵያ ኘሪሚየር ሊግ እግር ኳስ ውድድር የ2ኛ ዙር የተጫዋቾች ዝውውር ሰኞ የካቲት 16 ይጀምራል።

በዓለም አቀፋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ማህበር (ፊፋ) ደንብ መሠረት የእግር ኳስ ተጫዋቾች ዝውውር በየዓመቱ በሚካሄዱ ውድድሮች በሁለት ዙር ዝውውሩ ይከናወናል፡፡
የ1ኛ ዙር የተጨዋቾች የዝውውር ጊዜ የመጀመሪያው ዙር ውድድር ከመጀመሩ በፊት ተጀምሮ ለሦስት ወራት ብቻ የሚከናወን ሲሆን፣ የ2ኛው ዙር የዝውውር ጊዜ ደግሞ የመጀመሪያው ዙር ውድድር እንደተጠናቀቀ ተጀምሮ ለአንድ ወር ይካሄዳል፡፡

ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ኘሪሚየር ሊግ የ2ኛው ዙር የተጫዋቾች የዝውውር ጊዜ ከየካቲት 16 እስከ መጋቢት 16 ድረስ ለአንድ ወር የሚቆይ ይሆናል፡፡ ሀትሪክ ስፖርትም የዝውውር መስኮት ጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚከናወኑትን ዝውውሮች ወደናንተ የምናደርስ መሆኑ ከወዲሁ ለመግለፅ እንወዳለን።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor