የተጫዋቾች ምዝገባ የመረጃ አያያዝ ስልጠና ለፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ሊሰጥ ነው፡፡

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለሚሳተፉ ክለቦች የተጫዋቾች ዝውውር ምዝገባ (Transfer Match System) ባለሙያዎች የተጫዋቾች ምዝገባ የመረጃ አያያዝ በተመለከተ ለሁለት ቀናት የሚቆይ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ረቡዕ የካቲት 4/2012 መስጠት እንደሚጀምር አሳወቀ፡፡
ስልጠናው 16ቱም ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በስራቸው የሚገኙ ተጫዋቾችንና የክለቡ አባላትን መረጃ ወደ አለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ባዘጋጀው /FIFA Connect Platform/ የመረጃ ቋት ሙሉ መረጃ ማስገባት እንዲችሉ የሚያደርግና
በኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት አስተማማኝ እና የተሟላ የተጫዋች ምዝገባ መረጃን መያዝ የሚያስችል ሆኖ ይህ ስርዓት የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ የሀገር ውስጥ የዝውውር ስርዓቶችንና የተጨዋች መመዝገቢያ ስርዓቶችን በዓለም አቀፍ ዝውውሮችና ምዝገባዎች ወቅት ለግንኙነትና መረጃ ልውውጥ ምቹ ሁኔታዎችን የሚፈጥር ስርዓት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚገኙ 16 ክለቦች የሚሳተፉበት ስልጠና የካቲት 04 እና 05/2012 ዓ/ም ለሁለት ቀን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፅ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ የሚከናወን ይሆናል፡፡

via – EFF

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor