የብሔራዊ ስታዲየም ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ ለማስጀመር የሚያስችል የፊርማ ስነ ስርዓት በሸራተን አዲስ ተካሄደ ።

 

ለሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ እና ለማጠቃለያ ስራውን ለማከናወን 5.57 ቢሊዮን ብር እንደሚፈጅ ታውቋል ፡፡

መጋቢት 14/2012 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ገርጂ አካባቢ በቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ስራ ተቋራጭነት በMH ኢንጅነሪንግ አማካሪነት እየተገነባ የሚገኘው ብሔራዊ ስታዲየም በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ እየተገነባ ይገኛል ፡፡

የመጀመሪያው ምዕራፍ ከስታዲየሙ ሜዳ ሳር የማልበስና የመሮጫ ትራክ በስተቀር በውሉ መሠረት ሙሉ ለሙሉ ተጠናቋል ፡፡

ለዚህም 2.47 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል ፡፡

የሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ ለማስጀመር ኮሚሽኑ በዛሬው ዕለት ከተቋራጭ ድርጅቱ ጋር የፊርማ ስነ ስርዓት አካሂዷል ፡፡

የ2ኛው ምዕራፍ ግንባታ ለማካሄድ እና አጠቃላይ ስራውን ለመስራት 900 ቀናት ይፈጃል ተብሎ ይታሰባል ።

ብሔራዊ ስታዲየሙ ከ62 ሺ በላይ ተመልካች የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን በመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ከተካተቱት ውስጥ ከ30 በላይ የሚዲያ ክፍሎች፣ጋዜጣዊ መግለጫ አዳራሾች፣ የክብር እንግዶች ማረፊያዎች ፣ አሳንሰሮች ፣ የተለያዩ ደረጃቸውን የጠበቁ ካፌዎች እና ሬስቶራንቶች ፣ ከ1000 በላይ መፀደጃ ክፍሎች ፣የፍሳሽ ማስወገጃ ፣ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ተጠናቀዋል።

በሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ ከሚካተቱት ሥራዎች መካከል የመጫወቻ ሜዳውን ሳር ማልበስ፣ የመሮጫ ትራክ ማንጠፍ፣ የስታዲየሙን ጣሪያ ማልበስና ወንበር መግጠም ፣ሰው ሰራሽ ሀይቅ፣ የሄሊፕተር ማረፊያ፣ ዘመናዊ የደህንነት ካሜራ ፣ ሳውንድ ሲስተም ፣ የፓርኪንግ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች፣ የመለማመጃ ሜዳዎች እና ሌሎች ስራዎች የሚያጠቃልል ይሆናል ፡፡

የሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታውን ለማከናወን ከ5.57 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚፈጅ ታውቋል ።

ስታዲየሙን ሙሉ ለሙሉ ለማጠናቀቅ መንግስት ከ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ይሆናል።

አጠቃላይ ፕሮጀክቱም 48.8 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ስታዲየሙ ብቻውን 95,000 ካሬ ሜትር ይሸፍናል ፡፡

ምንጭ-ፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ገጽ…

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team