የባየር 2020 ወጣቶች ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ዛሬ ተጀመረ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የጀርመኑ ባየርሙኒክ እግር ኳስ ክለብ በጋራ ያዘጋጁት የ ”ባየር 2020 ወጣቶች ዋንጫ ማጣሪያ እግር ኳስ ውድድር ዛሬ የካቲት 19/2012 ዓ.ም ከቀኑ በ7፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በባየርሙኒክ እግር ኳስ ክለብ አዘጋጅነት በየዓመቱ በዓለም ላይ በሚገኙ ሀገራት መካከል የሚካሄደው የባየር ወጣቶች ዋንጫ ውድድር በዘንድሮ ዓመት ባየር 2020 ወጣቶች ዋንጫ በሚል የሚካሄድ ይሆናል፡፡

በዚሁ ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ የሚወዳዳደረውን ቡድን ለመምረጥ ጥሪ ከተደረገላቸው ከ2 ከተማ መስተዳድሮች እና ከ9ኙ ክልሎች የግል እና ከመንግሥት እግር ኳስ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ከ16 ዓመት በታች ታዳጊዎች የሚሳተፋበት የማጣሪያ ውድድር የካቲት 19 እና 20 /2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

በውድድሩ ከአዲስ አበባ ፣ ከቤኒሻንኑል፣ ከሱማሌ ፣ ከአማራ፣ ከደቡብ ፣ከኦሮሚያ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ እና ከሰውነት አካዳሚ የተውጣጡ 16 ቡድኖችን የሚያሳትፍ ሲሆን በእያንዳንዱ ቡድን (ፋትሳል ቡድን) 10 ታዳጊ ተጫዋቾች በአጠቃላይ 160 ታዳጊዎችን ተሳታፊ ያደርጋል፡፡
ቡድኖቹ በሁለት ምድብ በምድብ “ሀ” እና “ለ” ተከፍለው በእያንዳንዱ ምድብ በምድብ “ሀ” 8 ቡድኖች በምድብ “ለ” 8 ቡድኖች ተደልድለዋል፡፡

በሁለቱ ቀናት የጨዋታ ኘሮግራም
– ሐሙስ የካቲት 19 ቀን 2012 ዓ.ም በመክፈቻው እለት ከቀኑ በ7፡00 – 12፡00 ሰዓት በሚኖረው ጊዜ እያንዳንዱ ቡድን 7ጨዋታዎችን የሚካሄድ ሲሆን አንዱ ጨዋታ 10 ደቂቃዎችን የሚሸፍን ይሆናል፡፡ በአንድ የጨዋታ ጊዜ 4 ቡድኖች በግማሽ በግማሽ ሜዳ ጨዋታቸው ያደርጋሉ፡፡
በመጀመሪያው ቀን ጨዋታ ከ16ቱ ቡድኖች 8ቱ ቡድኖች ተለይተው የሚሸኙ ይሆናል፡፡


– ዓርብ የካቲት 20 /2012 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 እስከ 10፡30 ሁለት የግማሽ ፍፃሜ ውድድር በማድረግ የማጣሪያ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ፡፡
በእያንዳንዱ ጨዋታ የቴክኒክና ልማት ዳይሬክቶሬት እና የቴክኒክና ልማት ኮሚቴ ከባየርሙንክ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ምርጫውን የሚያካሂዱ ሲሆን በመጨረሻም ከየውድድሩ 10 የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተጫዋቾችን በመምረጥ የኘሮግራሙ ማጠቃለያ ይሆናል::

Via-EFF

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team