የባየርሙኒክ እግር ኳስ ክለብ ያዘጋጀው የእግር ኳስ አሰልጣኞች ስልጠና ዛሬ ተጀመረ፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጀርመኑ ባየርሙኒክ እግር ኳስ ክለብ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የ2ኛ ዙር የጀማሪ እግር ኳስ አሰልጣኞች ስልጠና ዛሬ የካቲት 9 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም መሰጠት ጀመረ፡፡


የተለያዩ ሥልጠናዎችን ለመስጠት ወደ አዲስ አበባ የገባው የባየርሙኒክ እግር ኳስ ክለብ ከየካቲት 9 – 13/2012 ዓ.ም ለአምስት ተከታታይ ቀን የሚቆየውን የ2ኛ ዙር የጀማሪ የእግር ኳስ አሰልጣኞች ስልጠና በዛሬው እለት መስጠቱን ጀምሯል፡፡ በዚሁ ስልጠና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል የጽሕፈት ቤት ኃላፊ እና የእግር ኳስ ልማት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሰለሞን ገብረስላሴ የመክፈቻው ኘሮግራም ባደረጉት ንግግር የባየርሙኒክ እግር ኳስ ክለብ ያዘጋጀው ይህ ስልጠና በእግር ኳሱ ላይ እየሰሩ ለሚገኙት ወጣት አሰልጣኞች እንዲሁም ለአገራችን እግር ኳስ እድገት ጠቃሚ በመሆኑ በተጨማሪም ባየርሙኒክ በቀጣይ ለመስጠት ባዘጋጃቸው የተለያዩ ስልጠናዎች በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስም አመስግነዋል፡፡


ሠልጣኞችም በመጀመሪያው ዙር የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ለዛሬው ስልጠና በመበቃታችሁ ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ አቅም እንደሚሆናችሁ ተስፋቸውን ገልፀው ስልጠናው በይፋ መጀመሩን አብስረዋል፡፡


ሥልጠናው በቪዲዮ የታገዘ የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠና ሲሆን በባየርሙኒክ እግር ኳስ ኘሮጀክት ለበርካታ ዓመት እያገለገሉ የሚገኙት የቀድሞው የባቫሪያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የታዳጊዎች እግር ኳስ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ሚ/ር ክርስቶፎ ሉክ እየተሰጠ ይገኛል፡፡ በዚሁ የሁለተኛው ዙር ስልጠና ቀደም ሲል በሁለት ምድብ በተካሄደው የጀማሪ እግር ኳስ አሰልጣኞች ስልጠና የተግባር ፈተናውን ያለፋ 30 አሰልጣኞች ተካፋይ ሆነዋል፡፡

Via – EFF

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor