የቅ/ጊዮርጊሷ የልብ ደጋፊ ካሰች መስቀሌ የቀብር ስነ- ስርዓቷ ዛሬ ተፈፅሟል

የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብን ለበርካታ ዓመታቶች በመደገፍ ትታወቃለች።ስሟም ካሰች መስቀሌ ይባላል። እሷ የክለቡ እንስት ደጋፊዎች እንዲበዙ ትልቁ አርዓያ ከሆኑት መካከል
ስሟ በጉልህ የሚጠቀስ ሲሆን በክለቡ የረጅም ጊዜ ደጋፊነቷ
ታሪክም ክለቧን ከልብ የምትወድ እና በህይወት ዘመኗም
ሌት ተቀን ሳትል በጉልበቷና በላቧ ቡድኗን በታማኝነት ማገልገሏም
ይታወቃል። ይህቺው አንጋፋ እና በቡድኑ ደጋፊዎች ዘንድ ሁሌም
ቢሆን በጣም የምትወደደው ካሰች ብዙዎቹ ሲጠሯት ካሱም
ይሏታል።

በህይወት ዘመኗ ክለቡ ትልቅ ደረጃ ላይ እንዲደርስ
በማሰብ ጠቃሚ የሆኑ ሀሳቦችን ፊት ለፊት ጭምር ለክለቡ
ደጋፊዎች በመናገር በብዙዎች ዘንድ የምትታወቅ እና የምትወሳ
ሲሆን ከዛም ውጪም ለኳስ ባላት ከፍተኛ ፍቅርና በማህበራዊ
ጉዳዮች ላይም ባላት ተሳትፎም ሁሉም ቦታ በመገኘት ጭምር
በራሷ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ብቻ ሳይሆን በሌሎች ክለብ
ደጋፊዎችም ጭምር በጣሙን የምትወደድም ናት።
የቅዱስ ጊዮርጊስ አንጋፋ ደጋፊ የሆነችው ካሰች መስቀሌ
በአዲስ አበባ ስታድየምም ሆነ በተለያዩ ሰፈር በመገኘት
የክለቡ ደጋፊዎች እንዲበዙ ትልቁን ስራ የሰራች ሲሆን በኳስ
ተመልካችነቷም ከራሷ ቡድን ደጋፊዎች ባሻገር ኢትዮጵያ ቡናን
ጨምሮ በኢትዮ ኤሌክትሪክ እና በሌሎች ቡድን ደጋፊዎችም
አክብሮት ያላት ናት።

በቅዱሰ ጊዮርጊስ ቡድን ደጋፊነቷ እና ውጤታማነት ደስተኛ
እንደሆነች የምትታወቀው ካሰች ከክለቧ ደጋፊነቷ በተጨማሪ
ኢትዮጵያ ቡና የሊጉን ዋንጫ በ2003 ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያነሳ
በክለቡ ፅ/ቤት በመገኘት ጭምር የአበባ እና የእንኳን ደስ
አላችሁ ፖስት ካርድም በመስጠት በቡድኑ ዘንድ ከፍተኛ ምስጋና
እንደቀረበላት ይታወቃል።

Editor at Hatricksport website

Facebook

መሸሻ ወልዴ

Editor at Hatricksport website