የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ ሰብሳቢ እና የካፍ ኢንተር ክለብ ኮምፒትሽን አባል የሆኑት ኢትዮጵያዊው አቶ አብነት ገ/መስቀል ካፍ ባደረገላቸው የክብር ግብዣ ትናንት ምሽት ወደ ጋቦን ተጒዙ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢሳ ሃያቱን ጨምሮ ከካፍ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ጤናማ ግንኙነት እየመሰረቱና ዕዉቅና እያገኙ የመጡት አቶ አብነት በጋቦን ቆይታቸው የሩብ ፍፃሜ እና የፍፃሜ ጨዋታን ከመከታተላቸው ውጪ ከካፍ ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር አ.አ ላይ ሰለሚካሄደው ምርጫና ዝግጅት እንደሚወያዩም ታውቋል ።
አስተያየት ይስጡ