የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ሥራ አመራር ቦርድ ውሳኔ አሳለፈ !

 

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሰበታ ከተማ መጋቢት 4 ቀን 2012 ዓ.ም በተጋጠሙበት ዕለት ከጨዋታው ፍፃሜ በኋላ ተጨዋቾች በክብር ትሪቡን በመውጣት ላይ እያሉ
1.ዮሴፍ ኪዳነማርያም
2.አማኑኤል መውጫ

የተባሉ የክለቡ አባላት ሆን ብለውና ተዘጋጅተው ሳላሀዲን ሰይድ የተባለውን ተጨዋች ከጀርባው መተውታል፡፡ ግለሰቦቹ ወዲያውኑ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወደ ለገሀር ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል፡፡

ይህን መሰል ጥቃት ከደጋፊዎች ይፈፀምብኛል ብሎ ያላሰበው ሳላሀዲን ሰይድ በንዴትና በቁጭት ውለታዬ ይሄ ይሁን ብሎ ከቁጥጥር ውጭ መውጣቱ ታይቷል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ሥራ አመራር ቦርድ መጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በጉዳዩ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ሁለቱም አባላት ልማደኛ አጥፊዎች መሆናቸውን በመገንዘብ፣ ርምጃ ካልተወሰደባቸው ሊያደርሱ የሚችለትን መጠነ ሰፊ ጥቃት በማጤን፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ11 የአባልነት ግዴታዎች
ማንኛውም አባል በተራ ቁጥር 11.3 የማህበሩን ዓላማዎች የሚፃረር፣ ወይም የማህበሩን ጥቅሞች የሚጐዳ፣ መልካም ስምና ዝናውን የሚያጠፋ ወይም ዓላማዎቹን የሚያደናቅፍ ማንኛውንም ተግባር ከመፈፀም መቆጠብ አለበት የሚለውን ጥሰው፣ አሳፋሪና አስነዋሪ ድርጊት በመፈፀማቸው በማህበሩ ደንብ ስለመውጣትና መወገድ በአንቀጽ 12 ተራ ቁጥር 12.2 በተደነገገው ላይ ሥራ አመራር ቦርዱ ከአባልነት ሊሰርዝ ወይም ሊያስወግድ ይችላል በሚለው መሠረት ሁለቱም አባሎች ከአባልነት እንዲሰረዙ ወስኗል፡፡

Via – st George fc offical page

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor