መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ ​የቅዱስ ጊዮርጊሱ አጥቂ  በልምምድ ላይ ጉዳትን አስተናገደ
ቅዱስ ጊዮርጊስየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

​የቅዱስ ጊዮርጊሱ አጥቂ  በልምምድ ላይ ጉዳትን አስተናገደ

አጋራ
አጋራ

የቅዱስ ጊዮርጊስንና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በአጥቂ ስፍራ በመምራት የላቀ ግልጋሎትን በመስጠት የሚታወቀው ሳላሃዲን ሰኢድ ትናንት በነበረው የክለቡ ማይነር ጌም ልምምድ ላይ የእግር ላይ ጉዳትን ሊያስተናግድ ችሏል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊሱ አጥቂ ሳላህዲን ሰኢድ  በተጨዋችነት ዘመኑ ሀገር ውስጥ ሲጫወት ለሙገርና ለቅዱስ ጊዮርጊስ   በርካታ ግቦችን ጤነኛም ሆኖ ጉዳት ላይም ሆኖ ግብ ሲያስቆጥር የነበረ ሲሆን በተጨዋችነት ዘመኑም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሊጉን ዋንጫዎች ከማንሳት ባሻገር በግሉም በ2000 ላይ ኮከብ ግብ አግቢ ተብሎ ተሸልሟል፡፡

ከእዚያ ውጪም በአፍሪካ ክለቦች የዘንድሮ ቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎም ለቅዱስ ጊዮርጊስ ውጤት ማማርና የ16ቱ ክለቦች የምድብ ድልድል ውስጥ መግባትም ትልቅ አስተዋፅኦ ከማድረጉ ባሻገር የውድድሩ ኮከብ ግብ አግቢ  በጋራ ሊሆንም ችሏል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊሱ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ሳላህዲን በትናንቱ የክለቡ  ልምምድ   ላይ  መጎዳቱ በእሁዱ ከመቐለ ከተማ ጋር በሚኖረው ጨዋታ ላይ መሰለፉን አጠራጣሪ ያደረገው ሲሆን የጉዳቱም መጠን ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገቢው ህክምና እየተደረገለት መሆኑም ተገልጿል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የሲዳማ ቡና ቡድን መሪ ታገደ

በዮሴፍ ከፈለኝ የፕሪምየር ሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና የቡድን መሪው የቀድሞው ዳኛ ዕግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...