መነሻ ገጽ ኢትዮጵያን በውጪ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድን ተጨዋቾች በደቡብ አፍሪካ የ ኢትዮጵያዊያንን የማሰባሰብ ማህበር አቋቋሙ�
ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

የቀድሞ የብሄራዊ ቡድን ተጨዋቾች በደቡብ አፍሪካ የ ኢትዮጵያዊያንን የማሰባሰብ ማህበር አቋቋሙ�

አጋራ
አጋራ

በይስሐቅ በላይ

ቀድሞ የኢትዮጵያ ብ/ቡድን
ውጤታማና ታዋቂ ተጨዋቾች
በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያዊያንን
በአንድ ጥላ ሥር የሚያሰባስብ በታሪክ
የመጀመሪያ የሆነ ማህበር በይፋ መሠረቱ፡፡
ለሐዋሳ ዱቄት፣ለአየር መንገድ፣ ለቅዱስ
ጊዮርጊስ፣ ለመድንና ለኢትዮጵያ ብ/ቡድን
በመጫወት የማይዘነጋ ውለታን የፈፀመው
ይልማ ተስፋዬ (ካቻማሊ)፣ ለሙገር፣
ለኢትዮጵያ ቡና፣ ለመከላከያና ለኢትዮጵያ ብ/
ቡድን በመጫወት ስሙ ከፍ ብሎ የሚነሳው
ማሞአለም ሻንቆ (አስኘሪላ) እንዲሁም ከአየር
መንገድ፣ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ከሐረር ቢራና
ከብ/ቡድኑ ውጤታ ማነት ጋር ስሙ አብሮ
የሚነሣው ፍቃዱ በላይ በጋራ በመሆን
በደቡብ አፍሪካ የመጀመ ሪያ የሆነውን
የስፖርት ማህበር በይፋ መስር ተዋል፡፡
ኢትዮጵያዊያን ስፖርቱን እንደ አንድ
ድልድይ በመቁጠር ከውድድር ባለፈ
በሀገራቸው ጉዳዮች ዙሪያ ስብስብ ብለው
የሚመክሩበት፣ባህልና ታሪካቸውን ለሌላው
አለም የሚያስተዋውቁበት፣የልምድና የተሞክሮ
ልውውጥ የሚያደርጉበት፣የሚረዳዱበት፣
አንድነታቸውን ይበልጥ የሚያጠናክሩበት
መድረክ ለመፍጠር በማሰብ ሶስቱ የቀድሞ
የብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ማህበሩን
ለመመስረት እንዳነሳሣቸው የማህበሩ
አሰባሳቢና ዳይሬክተር የሆነው ይልማ ተስፋዬ
(ካቻማሊ) በተለይ ለሀትሪክ ገልጿል፡፡
ከ33 አመታት በላይ ያስቆጠረው በሰሜን
አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽንና
የአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ስፖርት ፌዴሬሽን
አወቃቀርንና ልምድን በመውሰድ በደቡብ
አፍሪካ ተግባራዊ ለማድረግ በመንቀሳቀስ ላይ
የሚገኙት የቀድሞ የብ/ቡድናችን ባለውለተኞች
የኢትዮጵያዊያን የስፖርት ፌዴሬሽን በደቡብ
አፍሪካ ለመመስረት መነሳታቸውን ገልፀዋል፡፡
በተጨዋችነት ዘመናቸው ለክለቦቻቸውና
ለኢትዮጵያ ብ/ቡድን በየደረጃው በመጫወት
ሁሌም በስፖርት ቤተሰቡ በውጤታማ
እንቅስቃሴያቸው የሚታወሱት የቀድሞ
ባለውለተኞች ይልማ ተስፋዬ(ካቻ)፣ፍቃዱና
ማሞአለም ሻንቆ(አስኘሪላ) በብዙ መቶ ሺህ
የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በደቡብ አፍሪካ
ይኖራሉ እነዚህን ወገኖች በአንድ ጥላ ሥር
በማሰባሰብ የተለያዩ ውድድሮችን በየአመቱ
በማከናወን የሚገናኙበትን መድረክ ለመፍጠር
አስፈላጊውን ሁሉ አጠናቀናል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ የስፖርት ማህበር በደቡብ
አፍሪካ በመጪው ፌብሪዋሪ (የካቲት) ወር
የመጀመሪያውን ታሪካዊ ውድድር በፕሪቶሪያ
ከተማ ለመጀመር ከወዲሁ እየተንቀሳቀሱ
ሲሆን በዚህ ውድድርም ከሰባት እስከ ስምንት
የሚደርሱ ቡድኖች ይሣተፉበታል ተብሎም
ይጠበቃል፡፡


የኢትዮጵያ የስፖርት ማህበር በደቡብ
አፍሪካ መስራቾችና አዘጋጆች ውድድሩ በደቡብ
አፍሪካ ሕጋዊ ፍቃድ ያገኘና አስፈላጊውን
ፎርማሊቲ ያሟላ ሲሆን በቅርቡም በሀገሪቱ
የሚገኙ ውድድርችን በበላይነት ለሚመራው
የደቡብ አፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን(SAFA)
ለማሳወቅ ለተመሳሳይ ጉዳይ በሳምንቱ
መጨረሻ ወደ አዲስ አበባ ከመምጣቱ በፊት
ደብዳቤ ማስገባቱን ይልማ ተስፋዬ (ካቻ)
በተለይ ለሀትሪክ ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ስፖርት ማህበር በደቡብ
አፍሪካ አዘጋጆችና ከሶስቱ ዳይሬክተሮች
አንድ የሆነው ይልማ ተስፋዬ (ካቻ) “ማህበሩ
ከውድድር ባለፈ ትልቅ ሀገራዊ ፋይዳ
ያለው ነው” ካለ በኋላ “ከመሸናነፍ፣ዋንጫ
ከማግኘት በዘለለ ኢትዮጵያኖች በአንድ
ጥላ ስር ተሰባስበው በሀገራቸው ዙሪያ
የሚመክሩበት፣ባህልና ታሪካቸውን ይበልጥ
የሚያስተዋውቁበት፣ልምድና ተሞክሮ
የሚለዋወጡበት ከመሆኑም በላይ ለሀገር
ውለታ ውለው ያለፉ ነገር ግን በችግር ውስጥ
የወደቁ ባለውለተኞችን የመደገፍ፣ ወገንተኝነት
በግልፅ የሚንፀባረቅበት መድረክም እንዲሆን
ታስቦ ነው ማህበሩ የተቋቋመው” ብሏል፡፡
በቀጣይ ሣምንት የኢትዮጵያ የስፖርት
ማህበርን በደቡብ አፍሪካ ከመሰረቱት 3ቱ
የቀድሞ ተጨዋቾች አንዱ የሆነው ይልማ
ተስፋዬ (ካቻ) ለተመሳሳይ ሥራ አዲስ አበባ
የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ ሣምንት በማህበሩ
መመስረት ዙሪያና ስለ አጠቃላይ አላማው
በስፋት አነጋግረነው እናቀርባለን፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...