የስፖርቱ ባለውለተኞችን የተነጠቅንበት ጥቁር ሣምንት የእሸቴ ገበየሁ “ኳስ ፊደሉ” ህልፈት ብዙዎቹን አሳዝኗል

ያሳለፍነው ሣምንት የስፖርት ቤተሰቡን ለከፋ ሀዘን የዳረገ ጥቁር ሣምንት ሆኖ አልፏል፤በአትሌትክሱ መንደር ታላላቅ ድሎችን ለማስመዝገብ እየተንደረደረ ያለው በተለያዩ አለም አቀፍ
ውድድሮች በአጭር ርቀት ሀገሩን በመወከል ባንዲራዋ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ሲተጋ የነበረው አትሌት አባዲ ገና በለጋ እድሜው በድንገት በሞት የተነጠቀው ባሳለፍነው ሣምንት
ነው።በተጫዋችነትና በመከላከያ እግር ኳስ ክለብ ውስጥ በቴክኒክ ዳይሬክተርነትና በተለያየ ኃላፊነቶች በመስራት የሚታወቀው ዋስይሁን ማሞ በተመሳሳይ በሞት የተለየን በዚህ ባሳለፍነው
ሣምንት ነው። በኢትዮጵያ እግር ኳስ ትልቅ ስም ያለውና ስመ-ጥር ተጨዋቾችን በማፍራት የማይዘነጋ ውለታ ጥሎ ላለፈው ሰላማዊ ውቅያኖስና ሚችልኮትስ ለተባሉት ቡድኖች በመጫወት
ሁሌም በድንቅ ጥበቡ የሚደነቀውና የሚታወሰው “ኳስ ፊደሉና ጋሪንቻ” በሚለው ቅፅል ስሙም ተለይቶ የሚታወቀው እሸቴ ገበየሁ በጨካኙና በክፉው ሞት ተነጥቆ ለአንዴና ለመጨረሻ
ጊዜ ይህቺን አለም የተሰናበተውም ለስፖርት ቤተሰቡ ጥቁር ሳምንት ሆኖ ባለፈው በዚያው ሣምንት ነው፡፡
በሚያሳየው ጥበብ የተሞላበት ጨዋታው ከብዙዎች ከፍተኛ አድናቆት የተሰጠውና “ኳስ ፊደሉና ጋሪንቻ” የሚል ቅፅል ስም በጨዋታ ዘመኑ የወጣለት እሸቴ ገበየሁ ከብዙዎች
የመደነቁንና የመወደዱን ያህል በክለቦች ብቻ ተወስኖ የቀረና ሀገሪቱ ሳትጠቀምባቸው ካባከነቻቸው ተጨዋቾች አንዱ ነበር በማለት ብዙዎች በቁጭት ያስታውሱታል፡፡
የታላላቅ ስመ-ጥር ተጨዋቾች መፍለቂያ የነበረውና በኢትዮጵያ እግር ኳስ የማይዘነጋ ውለታን ከዋሉ ክለቦች አንዱ ለነበረው ሠላማዊ ውቅያኖስና ለሚችልኮስት በመጫወት ግቦችን
በስሙ በማስቆጠርና በርካታ የዋንጫ ሽልማቶችን በማግኘት የጨዋታ ዘመኑን ያጠናቀቀው እሸቴ ገበየሁ በወቅቱ በተደጋጋሚ በኮከብ ተጨዋችነትም ለሽልማት ይበቃ እንደነበር አብረውት
የተጫወቱና የቅርብ ጓደኞቹ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ፡፡
እሸቴ ገበየሁ የጨዋታ ዘመኑን ካጠናቀቀ በኋላም የአዲስ አበባ ጤና ስፖርት ማህበር እንዲመሰረት እንዲሁም የጤና ስፖርት ማህበሩ በሚመሰረትበት ወቅትም የራሱን የግል ድርጅት
ለረዥም ጊዜ በቢሮነት እንዲጠቀሙበት በመፍቀድ ትልቅ ውለታን ከዋሉ ሰዎች እንዱ ሲሆን የወድማማቾች አማኑኤል የጤና ቡድንን በተጨዋችነትና በአባልነት በማገልገልም አሳልፏል፡፡
የቀድሞ የሠላማዊ ውቅያኖስና የሚችልኮ ትስ ጥበበኛ ተጨዋች የነበረው እሸቴ ገበየሁ የቀድሞ ድንቅ ጥበቡንና ትዝታውን ጥሎ ወደዚህች ምድር ዳግም ላይመለስ ለአንዴና ለመጨረሻ
ጊዜ አሸልቧል፡፡
የእሸቴ ገበየሁ የቀብር ሥነ-ስርዓት መከ ኒሳ በሚገኘው አቦ ቤተክርስቲያን ጥር 27 ቀን 2012 ዓ.ም ቤተሰቦቹ፣ጓደኞቹ፣አብሮ አደጎቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹ፣የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ
ኢንስትራክተር አብርሃም መ ብራቱን ጨምሮ በርካታ ታላቅ የስፖርት ቤተ ሰቦች በተገኙበት በክብር ተፈፅሟል፡፡

Hat-trick Weekly Sport Newspaper Founder & Managing Editor.
The First Color Sport Newspaper in the country.

Yishak belay

Hat-trick Weekly Sport Newspaper Founder & Managing Editor. The First Color Sport Newspaper in the country.