የሞገስ ታደሰ የቀብር ስነስርዓት ዛሬ ተፈፅሟል

በህመም ምክንያት ትናንት  ማክሰኞ ከቀኑ 6:30 በሞት ከዚህ አለም የተለየው ሞገስ ታደስ ዛሬ በቀጨኔ ደብረሰላም መድሀኒአለም ቤተክርስትያን ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት የቀብር ስነስርአቱ  ተፈፅሟል።

 

1983 ዓ/ም አዲስ አበባ በጃንሜዳ አካባቢ የተወለደው የቀድሞ ተጫዋች ሞገስ ታደሰ። ባጋጠመው የጤና እክል በየካቲት 12 ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በትላንትናው ዕለት የካቲት 05/2012 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ባጋጠመው የጤና እክል ምክንያት ለማሳከም እና ወደ ቀድሞ ጤንነቱ ለመመለስ በርካታ የስፖርት ቤተሰቦች ርብርብ ማድረጋቸው ይታወቃል።

ሞገስ ታደሰ ከቅዱስ ጊዮርጊስ C ቡድን ጀምሮ እስከ ዋናው ቡድን እንዲሁም ሲዳማ ቡና፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ አዳማ ከተማ፣ ወልዲያ ከተማ የተጫወተ ሲሆን ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ቡድን በመጫወት። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ስታልፍ የቡድኑ አባልም ነበር።

ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እና ድህረ-ገፅ በሞገስ ታደሰ ህልፈት  የተሰማትን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀች ለቤተሰቡ እና ወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለስፖርት ቤተሰቡ መፅናናትን ትመኛለች።

Managing Editor at Hatricksport Website

FacebookTwitterGoogle+YouTube

ሙሴ ግርማይ

Managing Editor at Hatricksport Website