የመቐለ 70 እንደርታ የመጀመሪያው ዙር ጉዞ ሲዳሰስ

 

የሊጉ መጠናቀቅ ተከትሎ የተለያዩ ክለቦች የመጀመሪያው ዙር ጉዞ ምን ይመስላል የሚለውን ነገር እያነሳን ቆይተናል በዛሬው ፅሁፋችን ደግሞ የአምናው champion መቀለ 70 እንደርታ የመጀመሪያውን ዙር ጉዞ ምን ይመስል ነበር የሚለውን እንዳስሳለን።

በአሰልጣኝ ገ/መድህን ሃይሌ እየተመሩ በ25 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ይዘው የመጀመሪያውን ዙር ያጠናቀቁት ምዓም ኣናብስቶቹ ከሜዳቸው ውጪ ለማሽነፍ ሆነ ነጥብ ይዞ ለመውጣት ስቸገሩ የመጨረሻውን ዙር አጠናቀዋል። ከነበራቸው ችግር አንፃር የያዙት ነጥብ ከመሪዎቹ ጋር ሲነፃፀር ግን በጣም ጥሩ የሚባልላቸው ምዓም ኣናብስቶቹ። በተደጋጋሚ ኳስ ይዞ በመጫወት እና ማጥቃት ላይ የተመረኮዘ ፈጣንና ማራኪ ቅብብሎች በማድረግ ኳሶችን ወደ ፊት አጥቂዎቻቸው ኦኪኪ እና አማኑኤል በማድረስ የግብ አጋጣሚ በመፍጠር በመጀመሪያው ዙር ሲከተሉት የነበረው የጨዋታ ስልት ነው።

መቐለ 70 እንደርታ ካደረጓቸው 15 ጨዋታዎች 8 አሸንፎ በ6 ሲሸነፉ በቀሪ 1 ጨዋታ ነጥብ ተጋርተዋል። በሜዳቸው ካደረጓቸው 8 ጨዋታዎች ስድስቱን በድል ሲወጣ በአንድ ተሸንፎ በቀሪ አንድ ደግሞ ነጥብ ተጋርቷል። ይህም ማለት መቐለ 70 እንደርታ በመጀመሪያው ዙር ያስመዘገቧቸውን የስምንት ጨዋታዎች ድል በሜዳቸው እና ከሜዳቸው ውጪ ነው። በሜዳቸው ባደረጉት ጨዋታ በተጋጣሚ መረብ ላይ 14 ግቦችን ማሳረፍ ሲችሉ በተቃራኒው 6 ግቦች ተቆጥረውባቸዋል። መቐለ 70 እንደርታዎች በሜዳቸው የሚያደርጉት ጨዋታ ላይ ግብ ያስቆጥራሉ ግብም ይቆጠርባቸዋል። በሜዳቸው በሚያደርጉት እያንዳንዱ ጨዋታ ላይ 1.5 ግቦችን ሲያመርቱ 0.4 በአንፃሩ በአማካይ ይቆጠርባቸዋል።

መቐለ 70 እንደርታዎች ከሜዳቸው ውጭ ባደረጓቸው 7 ጨዋታዎች በአምስቱ ተሸንፎ በሁለቱ አሽንፎል። ይህ የሚያሳየው ደግሞ ከሜዳው ውጭ ለማሸነፍ እንደሚከብዳቸው ነው። ከሜዳው ውጭ ባደረገው ጨዋታ 6 ግብ ሲያስቆጥር 9 ግብ ተቆጥሮበታል። ከሜዳው ውጪ ስጫወቱ ነጥብ ይዘው ለመውጣት ሚከብዳቸው የመከላከል አቅማቸው ደካማ ብለን ልንወስደው የምንችል ነው። መቐለ 70 እንደርታዎች ኳስ ይዘው በመጫወትና በማጥቃት ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል ቢደርሱም የፊት መስመራቸው ከሜዳው ውጭ ግብ ለማስቆጠር ያዳግተዋል። መቐለ 70 እንደርታዎች በአጣቀላይ በመጀመሪያው ዙር በአጠቃላይ በተጋጣሚቻቸው ላይ 20 ግቦችን አግብተው 15 ገብቶባቸዋል። በየጨዋታው 0.8 ግቦችን ሲያገቡ በአንፃሩ 0.6 ይቆጠርባቸዋል። ይህ ደግሞ ግብ የማያገባ እና ግብ የማይገባበት መቐለ 70 እንደርታ ብለን እንድናነሳ ያደርገናል። በመጀመሪያው ዙር ከሜዳቸው ውጪ ባህርዳር 3-2 ሺያሽንፉ ከፍተኛ ግብ የተቆጠረበት ብቸኛው ጨዋታ ሲሆን። በሜዳቸው 5-1 አዋሳ ያሸነፉበት ደግሞ ለምዓም አናብስቶቹ በመጀመሪያው ዙር ያሳኩት ጣፋጭ ድል ነው። በስምንት ጨዋታዎች ግብ ሳይቆጠሮባቸውም ሳያስቆጥሩም ወጥተዋል። አማኑኤል ገ/ሚካኤል እና ኦኪኪ አፎላቢ ስድስት ስድስት ግቦችን በማስቆጠር የመጀመሪያው ዙር የቡድኑ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ናቸው።

መቐለ 70 እንደርታዎች ባለፈው አመት የመጀመሪያው ዙር በአንደኛ ደረጃን ነበር ይዞ ያጠናቀቀው። ዘንድሮ በቅድስ ጊየርግስ እና ፋሲል ከነማ ተበልጦ በሶስተኛ ይከተላቸዎል።

የቡድኑ ጠንካራ እና ደካማ ጎን

ቡድኑ ግብ ማስቆጠር የሚችል ጠንካራ የአጥቂ መስመራቸው እንደ ጠንካራ ጎኑ ሲነሳ። የተከላካይ አማካይ(defence midfielder)በአንፃሩ ለግብ የሚሆን ኳሶችን በመፍጠር እና ወደሆላ ተመልስው ተከላካይን ማገዝ ላይ እንደ ድክመት ሊታይ የሚችል ነው።

በሁለተኛው ዙር የሚጠበቅባቸው

ምንም እንኳን ከአጨዋወት ጋር አሪፍ ቢሆንም ግን የ አማካይ እና ተከላካይ ቦታ ላይ ለቡዱኑ ጥንካሬ አዲስ ሃይል ሊስጡ የሚችሉ ተጫዎቶች ብያስፈርሙ የአምናው ዋንጫ እንደሚደግሙት አያጠራጥርም ። በተለይ በመጨረሻዎቹ ጨዋታዎች ላይ ያሳየው የቡድኑ አጨዋወት ለአይን ማራኪ እና አሽንፈው ለመውጣት ሚያረጉት ጥረት የሚደነቅ ነው። በተጨማሪም የአጥቂ መስመራቸውን ተቀናጅተው በመስራት በሁለተኛው አስተካክለው የሚመጡ ከሆነ ጠንካራ ተፎካካሪ እና የአምናው ዎንጫ የመድገም አቅም እንዳላቸው ማየት ችለናል።

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team