የሐትሪክ ስፖርት የጨዋታ ኮከብ – ኦኪኪ አፎላቢ

ይህ የሀትሪክ ስፖርት የጨዋታ ኮከብ ምርጫ ጨዋታውን በሚመለከቱ ሪፖርተሮች ተጫዋቾች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ማእከል አድርጎ የሚከናወን ምርጫ ነው።

ትግራይ ስታድየም ላይ የተካሄደው የመቐለ 70 እንደርታና የሀዋሳ ከተማ ጨዋታ በባለሜዳዎቹ ከፍተኛ ብልጫ አሸናፊነት መጠናቀቁ ይታወሳል። ሀትሪክ ስፖርትም ክለቡ መቐለ 70 እንደርታ ከተከታታይ ሁለት ሽንፈቶች በኃላ ወደ ድል እንዲመለስ ከፍተኛ ድርሻ የነበረውን ናይጀርያዊ አጥቂ ኦኪኪ ኦፎላቢን የጨዋታው ኮከብ ብላ መርጣለች።

ጨዋታው ላይ ሥስት ግቦችን አስቆጥሮ ሀትሪክ መስራት የቻለው ኦኪኪ ኦፎላቢ ከግቦቹ በተጨማሪ መደ መሀል እና መስመር እየወጣ ከሌሎች የቡድኑ አጋሮቹ ጋር የነበረው ቅንጅት የሀዋሳ ተጨዋቾችን ያስቸገረ ነበር።

 

Hatricksport website writer

Twitter

ዳዊት ብርሀነ

Hatricksport website writer