20ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ዛሬም ቀጥሎ ሲውል የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሽንፈት አስተናግዷል።
አዳማ ከተማ በሜዳው ቅዱስ ጊዮርጊስን አስተናግዶ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። ዳዋ ሁቴሳ በ81ኛው ደቂቃ በቀድሞ ክለቡ ላይ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ አስቆጥሯል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ባለፈው ሳምንት በመከላከያ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት መሸነፉ አይዘነጋም።
ፈረሰኞቹ ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎችን በመሸነፋቸው ከደደቢት ጋር የነበራቸውን የነጥብ ልዩነት ማስፋት ሳይችሉ ቀርተዋል።
በአንፃሩ አዳማ ከተማ ደረጃውን ማሻሻል ችሏል።
በሌላ ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ ሃዋሳ ከተማን ያስተናገደው መከላከያ 3 ለ 0 ተሸንፏል።
ጋዲሳ መብራቱ በ22ኛው እና 46ኛው ደቂቃ እንዲሁም ጃኮ አራፋት በ2ኛው ደቂቃ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
አርባ ምንጭ ላይ ደግሞ አርባ ምንጭ ከተማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ያደረጉት ጨዋታ በባለሜዳው ክለብ 2 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል።
ፀጋዬ አበራ እና አማኑኤል ጎበና ግቦቹን ከመረብ አዋህደዋል።
በነገው እለት ደግሞ በሃዋሳ ስታዲየም በቡና ደርቢ፥ ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ቡና ይጫወታሉ።
ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ 35 ነጥብ ይዞ ሲመራ፥ ደደቢት በተመሳሳይ ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ ይከተላል።
አዳማ ከተማ በ20 ጨዋታ 34 ነጥብ ይዞ 3ኛ፣ ሲዳማ ቡና በ19 ጨዋታ 33 ነጥብ በመሰብሰብ 4ኛ እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና በተመሳሳይ ጨዋታ 32 ነጥቦች በመያዝ ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አዲስ አበባ ከተማ በ20 ጨዋታ በተመሳሳይ 15 ነጥቦች የደረጃውን ግርጌ ይዘዋል።
ከፍተኛ ግብ አግቢነቱን የደደቢቱ ጌታነህ ከበደ በ16 ጎሎች ሲመራ፣ ሳላዲን ሰይድ፣ ፍፁም ገብረማርያም እና አዳነ ግርማ በእኩል 9 ጎሎች ይከተላሉ።
የደረጃ ሰንጠረዥና ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎችን ይመልከቱ፡፡
| # | ክለብ | ተጫ | ልዩ | ነጥብ |
|---|---|---|---|---|
| 1 | ቅዱስ ጊዮርጊስ |
19 | 18 | 35 |
| 2 | ደደቢት |
20 | 11 | 35 |
| 3 | አዳማ ከተማ |
20 | 5 | 34 |
| 4 | ሲዳማ ቡና |
19 | 5 | 33 |
| 5 | ኢትዮጵያ ቡና |
19 | 10 | 32 |
| 6 | ፋሲል ከተማ |
19 | 5 | 29 |
| 7 | አርባምንጭ ከተማ |
20 | 3 | 28 |
| 8 | ሀዋሳ ከተማ |
20 | 0 | 24 |
| 9 | 20 | -1 | 24 | |
| 10 | መከላከያ |
20 | -9 | 24 |
| 11 | ኢትዮ ኤሌክትሪክ |
20 | -1 | 23 |
| 12 | ወላይታ ድቻ |
20 | -7 | 22 |
| 13 | ድሬዳዋ ከተማ |
20 | -8 | 21 |
| 14 | ጅማ አባቡና |
20 | -4 | 20 |
| 15 | አዲስ አበባ ከተማ |
20 | -9 | 15 |
| 16 | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ |
20 | -15 | 15 |
















አስተያየት ይስጡ