የሉሲዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የሚያደርግበት ቀን ታውቋል

የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ 2020 የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታ ከጅቡቲ ሴት ቤሔራዊ ቡድን ጋር የተደለደለችው ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጨዋታውን የምታደርግበት ቀን ታውቋል።

 

ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የአራት ጨዋታ ጊዜ ብቻ የሚቀረው የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከጅቡቲ አቻው ጋር የመጀመሪያውን የማጣሪያ ጨዋታ በባህርዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ.ም የሚያከናውን ሲሆን የመልሱ ጨዋታ ከስምንት ቀናት በኃላ ሚያዝያ 6 ቀን 2012  ጅቡቲ ላይ እንደሚከናወን ለማወቅ ተችሏል።

 

የኢትዮጵያ የሴቶች ቤሔራዊ ቡድን በማጣርያው የጅቡቲ አቻውን ማሸነፍ ከቻለ የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድንን ግንቦት 24 ቀን 2012 ሞሮኮ ላይ የሚገጥም ይሆናል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor