የሀዲያ ሆሳዕና ክለብ ቴክኒካል ዳይሬክተር ደቡብ አፍሪካ ስለሚገኙ ከወላይታ ድቻ ጋር ቢሚኖረው ጨዋታ ቡድኑ በህክምና ባለሞያው ብቻ እየተመሩ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

 

በ13ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሜዳው ወላይታ ድቻን የሚያስተናግደው ሀድያ ሆሳዕና የክለብ ቴክኒካል ዳይሬክተር ፍቅረየሱስ ዳንኤል በትምህርት ጉዳይ ደቡብ አፍሪካ ስለሚገኙ በህክምና ባለሞያው ቢኒያም ተፈራ እየተመሩ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በትላንትናው ዕለት በቡድኑ ቦርድ ውሳኔ መሰረት አሰልጣኙ ግርማ ታደሰን እና ረዳቶቹን መታገዳቸው ተከትሎ በአንዳንድ ሚዲያዎች ሀድያ ሆሳዕና በህክምና ባለሞያው ቢኒያም ተፈራ እና በከለቡ ዳይሬክተር ፍቅረየሱስ ዳንኤል። እየተመራ ወላይታ ድቻን ይገጥማል የሚሉ ወሬዎቹ በስፋት እየተዘገበ ይገኛል ይህም ፍፁም የተሳሳተ መሆኑን ሀትሪክ ስፖርት ከክለቡ ቴክኒካል ዳይሬክተር ፍቅረየሱስ ዳንኤል ጋር በነበራት አጭር ቆይታ ማረጋገጥ ችላለች።

ሀትሪል ስፓርት ከ ሀድያ ሆሳዕናው ቴክኒካል ዳይሬክተር አቶ ፍቅረእየሱስ ጋር ያደረገችው አጭር ቆይታ።

በቀጣዩ ጨዋታ ቡድኑን በአሰልጣኝነት እየመራህ ወደሜዳ ትገባለህ?

በፍፁም እኔ አሁን ደቡብ አፍሪካ ነው ያለሁት የህክምና ባለሙያው ቢኒያም ተፈራ ቡድኑን እየመራ ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል። መንገድ ላይ ስለነበርኩ አዲስ ነገር ካለ እርግጠኛ አደለሁም።

ደቡብ አፍሪካ በምን ጉዳይ ነው የሄድከው?

የፒኤች ዲ (PHD) ትምህርት ለማጠናቀቅ ነው የሄድኩት።

እና ገና ዶክተር አልተባልክም ማለት ነው?

አዎ! ገና የPHD ትምህርቴን እየተከታተልኩ ነው። አንዳንድ ሚዲያዎች ላይ ዶክተር ፍቅረየሱስ እየተባለ ያለው ነገር ትክክል አይደለም።