የሀዘን ዜና | ፌዴራል ረዳት ዳኛ ብርሃኑ ኢቱ በመኪና አደጋ ህይወቱ አለፈ ….

 

ቦሌ አራብሳ ከሚገኘው ቤቱ ለልምምድ የወጣው አርቢትሩ ከወጣበት ሳይመለስ ቀርቷል፡፡ በደረሰበት የመኪና አደጋ ህይወቱ ያለፈው ረዳት ዳኛ የከፍተኛ ሊግን በሙያው ሲያገለግል ቆይቷል፡፡አሁን በቅርብ ጓደኞቹ በተገኘ መረጃ አስክሬኑ ለምርመራ ምኒሊክ ሆስፒታል ይገኛል ተብሏል፡፡

በከፍተኛ ሊግ ረዳት አርቢትር ሆኖ ሲያገለግል የነበረው ፌዴራል ረዳት ዳኛ ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት ነበር፡፡ ሀትሪክ ስፖርት  በረዳት ፌዴራል አርቢትር ብርሃኑ ህልፈት የተሰማንን ሀዘን እየገለጽን ለባለቤቱ ለቤተሰቦቹ ለጓደኞቹና ለቅርብ ሰዎቹ መጽናናትን እንመኛለን፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport