የሀትሪክ ስፖርት የሳምንቱ ምርጥ 11

 

የ 14ኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ምርጥ 11 ጨዋታውን በተመለከቱ ሪፖርተሮቻችን ምርጫ እና ባቀረቡት አሳማኝ ምክንያት ብሎም በሚሰጧቸው ነጥቦች የተመረጡ ናቸው።

አሰላለፍ – 3-4-3

ግብ ጠባቂ

ፍቅሩ ወዴሳ (ሲዳማ ቡና)

ቡድኑ ሲዳማ ቡና ወልቂጤ ከተማን ከሜዳው ውጭ ነጥብ ይዞ እንዲወጣ ከፍተኛ ድርሻውን ይወስዳል። በተለይ በሁለተኛው አጋማሽ ባለሜዳዎቹ ጫና ፈጥረው በሚጫወቱበት ወቅት የፈጠሯቸውን በርካታ ግብ የሚሆኑ አጋጣሚዎችን አድኗል።

ተከላካይ

ስዩም ተስፋዬ መቐለ 70 እንደርታ

መከላከል እና ማጥቃት ላይ ተመጣጣኝ ተሳትፎ የነበረው ስዩም ተስፋዬ በዚህ ሳምንት ጎልተው ከመጡ ተጨዋቾች መሀል ሚጠቀስ ነው።በመከላከሉ ረገድ በግራ መስመር የተሰለፈውን የየተሻ ግዛውን እንቅስቃሴ በሚገባ መቆጣጠር የቻለው ስዩም ተስፋዬ በተጨማሪ ኦኪኪ ኦፎላቢና(የጨዋታው የመጀመርያ ግብ) ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊስ ያስቆጠሩዋቸውን ግቦች አመቻችቶ ማቀበል ችልዋል።

አዲሱ ተስፋዬ (ሰበታ ከተማ)

ቡድኑ ሰበታ ቡናን ሲገጥም ተጫዋቹ ታይሚንግ ላይ በጣም ጥሩ ነበር። ቡናዎች በማጥቃት እንቅስቃሴ ላይ ሲሆኑ ማርክ የሚያደርግበት ሁኔታ እንዲሁም ቡድኑ በሚያደረገው የማጥቃት እንቅስቃሴ ላይ ጉልህ የሆነ ሚና ነበረው :: ሰበታ ኳስ ከኋላ መስርተው በሚወጡበት ጊዜ አስፍቶ በመጫወት እራሱን ከጫና የሚያወጣበት መንገድ ጥሩ ነበር።

በረከት ሳሙኤል (ድሬዳዋ ከተማ)

ከውድድር ዓመቱ መጀመር አንስቶ በጥሩ ብቃት ላይ የሚገኘው በረከት ሳሙኤል በዚህ ሳምንትም ቡድኑ ወደ ጅማ ተጉዞ ባደረገው ጨዋታ ጥሩ እንቅስቃሴ በማድረግ በሳምንቱ ምርጡ መካተት ችሏል። በጨዋታው ምንም እንኳ ቡድኑ ጅማ አባጅፋር 2-1 ውጤት ቢያሸንፍም ተጋጣሚው በድን ብልጫ ወሰዶ እንዳይጫወት እና ድንቅ የቅቅጣ ትምት ጎልም አስቆጥሯል።

አማካይ

ሱራፌል ዳኛቸው(ፋሲል ከተማ)

ጎንደር አፄ ፋሲለደስ ስታድየም ላይ የተካሄደው ተጠባቂው የፋሲል ከነማ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ በአቻ ውጤት መጠናቀቁ ይታወሳል። በጨዋታው ፋሲል ከነማ ከመመራት ተነስቶ አቻ እንዲለያይ የአመካይ ስፍራ ተጫዋቹ ከፍተኛ ሚና ከመጫወቱም በላይ። ሁለተኛውን ግብ ሙጂብ ቃሲም በፍፁም ቅጣት ምት ሲያስቆጥር ለፍፁም ቅጣት ምቱ መገኘት ምክንያት ነበር። በተጨማሪም ከቡድን አጋሮቹ ጋር የነበረው ቅንጅት የቅዱስ ጊዮርጊስ ተከላካዮችን ያስቸገረ ነበር።

ንጋቱ ገ/ስላሴ(ጅማ አባ ጅፋር)

በሦስት የአማካይ መስመር ተጨዋቾች ለሚጫወተው የጳውሎስ ጌታችው ቡድን የንጋቱ ገ/ሥላሴ ጎላ ያለ ነው። በተለይ ቡድኑ ድሬን አስተናግዶ በረታበት ጨዋታ ንጋቱ የሳይው እንቅስቃሴ ቡድኑን እጅግ ጠቅሟል። አልክስ አሙዙ የቀይ ካርድ ሰለባ ከሆነ ቦሀላ ወደ ዋላ በመመለስ የተከላካይ ክፍልን ከድር ተቀይሮ እስኪገባ ድረስ በመከላከሉ ረገድ ሚዛኑን እንዳይስት ያደርገው ጥረት እና የመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴዎችን የሚያስጀምረበት ሂደት ውጤታማ ነበር።

ከንዓን ማርክነህ(አዳማ ከተማ)

አዳማ ከተማ ከተማ ወልዋሎን በመርታት ተከታታይ የሜዳ ላይ ድሉን ሲያስመዘግብ ተጫዋቹ ተቀይሮ እስከወጣበት ደቂቃ ድረስ ለቡድኑ የማጥቃት እንቅስቃሴ ቁልፍ ሚናን ሲጫወት ነበር። ከንአን ማርክነህ ተቀይሮ ከወጣ በሃላ የቡድኑ የማጥቃት እንቅስቃሴ እንዲቀዛቀዝ ያደረገው ሁነት የተጫዋቹ ድንቅ እንቅስቃሴ ማሳያ ነበር።

ጋዲሳ መብራቴ(ቅዱስ ጊዮርጊስ)

ተጫዋቹ አቻ የምታደርገው ግብ ከማስቆጠሩም በተጨማሪ በርካታ የግብ እድሎችን የፈጠረ ሲሆን። ከአቤል እና አሜ መሀመድ ጋር የነበረው ጥምረት ተከላካዮችን ሲረብሽ ነበር። ተጎድቶ ባይወጣ ምናልባትም ግብ የማስቆጠር እድሎች የመፍጠር አጋጣሚው ከፍተኛ ነበር።

አጥቂዎች

ኦኪኪ አፎላቢ(መቐለ 70 እንደርታ)

አቋሙ ወርዷል ተብሎ ብዙ ትችት ሲሰነዘርበት የነበረው ተጫዋቹ በዚህ ሳምንት ቡድኑ ከተከታታይ ሽንፈት በኋላ ሶስት ግቦችን አስቆጥሮ ሀትሪክ በመስራት ወደ አሸናፊነት መመለስ ችሏል። ከዛ በተጨማሪም ከአጣማሪዎቹ የሚላኩለት ኳሶች ወደ ውጤታማነት መቀየሩ የሳምንቱ ምርጥ ውስጥ እንዲካተት አድርጎታል።

ኤርሚያስ ኃይሉ(ጅማ አባ ጅፋር)

ጅማ አባጅፋር ድሬዳዋ ከተማን በጎደሎ ተጫዋቾች 2-1 ባሸነፈበት ጨዋታ። ተጫዋቹ እስከተቀየረበት ደቂቃ ድረስ ለቡድኑ የማጥቃት እንቅስቃሴ ቁልፍ ሚናን ከመጫወቱም በተጨማሪ ለተቆጠሩት ሁለት ግቦች ቀጥተኛ ተሳትፎም ነበርው።

ይገዙ ቦጋለ (ሲዳማ ቡና)

ሲዳማ ቡና ከሜዳው ውጭ ሙሉ ሶስት ነጥብ ይዞ እንዲወጣ ያገኛትን አጋጣሚ በሚገባ ወደ ግብ ቀይሮ ቡድኑ ተከታታይ ሶስት ነጥብ እንዲያስመዘግብ ማድረግ ችሏሌ። በተጨማሪም ከአጣማሪዎቹ ጋር ጥሩ ተግባቦትን በመፍጠር የሳምንቱ ምርጥ ውስጥ እንዲካተቱ አድርጓቸዋል።

ተጠባባቂዎች

አብዱልአዚዝ ኬይታ
ሙልጌታ ወልደጊዮርጊስ
ታፈሰ ሰለሞን
አቤል ያለው
ሙጂብ ቃሲም
በረከት ደስታ

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team