መነሻ ገጽ ዜናዎች ዜና | የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ1ኛ ዙር ግምገማ ዛሬ ተካሄደ።
ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ዜና | የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ1ኛ ዙር ግምገማ ዛሬ ተካሄደ።

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ1ኛ ዙር ግምገማ በፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ ክለቦች ተወካዮች እና በፌደሬሽኑ አመራሮች ዛሬ የተካሄደ ሲሆን በውድድር ጊዜው የነበሩ በጎ ጎኖች እና የተስተዋሉ ችግሮች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት አካሂዷል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ በፌደሬሽን ፕሬዝደንት አቶ ጁነዲን ባሻ የተጀመረው ግምገማ ስለ ዳኝነት ስለ ስፖርታዊ ጨዋነት የሁለተኛው ዙር ስለሚጀመርበት ቀን እና የጥሎ ማለፍ ድልድል የተነሱ ጉዳዮች ነበሩ። አቶ ጁነዲን በንግግራቸው ሁሉም ዳኞች ላይ እጅ መቀሰሩን ትቶ የየራሱን ሀላፊነት መወጣት አለበት ሲሉ ሀሳብ ሰጥተዋል። ከዚህም በማስቀጠል የውድድር ስነስርአት ኮሚቴ ተወካይ አቶ ከበደ ወርቁ የአንደኛ ዙር ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በርከት ያሉ ቁጥራዊ መረጃዎችን አስደግፈው አቅርበዋል።

የጥሎ ማለፉ ውድድር በምን አይነት አካሄድ መጓዝ አለበት በሚለው ሀሳብ ላይ የየክለቦቹ ተወካዮች ሀሳብ የሰጡበት ሲሆን የከፍተኛ ሊግ እና የአንደኛ ሊግ ክለቦች በውድድሩ እንዲሳተፉ ጥሪ ቢደረግላቸውም ምላሽ የሰጠ ክለብ ባለመኖሩ የጥሎ ማለፉ ውድድር በፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ ክለቦች መካከል ብቻ ለማድረግ ተወስኗል። ከዚህ በተጨማሪም አንዳንድ ክለቦች ባቀረቡት ቅሬታ መሰረት የሁለተኛው ዙር ጨዋታዎች የሚጀምሩበት ቀን ይራዘምልን ብለው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት መጋቢት 8 2010ዓ.ም ይጀምራል ተብሎ የነበረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2ኛ ዙር ጨዋታዎች በአንድ ሳምንት ተራዝሞ መጋቢት 15 2010 ዓ.ም እንዲጀምር ተወስኗል።

በተያያዘም በዚሁ እለት እጣው የወጣለት የጥሎ ማለፍ ውድድር ተጋጣሚዎች ከዚህ የሚቀጥለው ነው።

1) ኢ/ቡና ከወልዲያ (አዲስ አበባ )
2) ወልዋሎ ከ አርባምንጭ (አዲግራት)
3) ፋሲል ከ አዳማ (ጎንደር )
4) መከላከያ ከ ድሬደዋ (አዲስ አበባ )
5) ጅማአባጅፋር ከ ደደቢት (ጅማ)
6) ኤሌክትሪክ ከ መቀለ (አዲስ አበባ)
7) ሀዋሳ ከሲዳማ (ሀዋሳ)
8) ቅ/ጊዮርጊስ ከ ወላይታ ድቻ(አዲስ አበባ)

የእነዚህ 8ጨዋታዎች አሸናፊዎች ወደ ሩብ ፍፃሜ በማለፍ በወጣላቸው ድልድል መሰረት ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

9) የጨዋታ ቁጥር 1 አሸናፊ ከ ጨዋታ ቁጥር 2 አሸናፊ

10) የጨዋታ ቁጥር 3 አሸናፊ ከ ጨዋታ ቁጥር 4 አሸናፊ

11) የጨዋታ ቁጥር 5 አሸናፊ ከ ጨዋታ ቁጥር 6 አሸናፊ

12)የጨዋታ ቁጥር 7 አሸናፊ ከ ጨዋታ ቁጥር 8 አሸናፊ

የጥሎ ማለፉ ውድድር ቀን እና ሰአት ወደፊት ይገለፃል ተብሏል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...