መነሻ ገጽ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜና እረፍት |የደደቢቱ አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ በድንገት ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግደደቢትድንገተኛ ዜና

ዜና እረፍት |የደደቢቱ አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ በድንገት ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

አጋራ
አጋራ

ረጅም አመታትን በአሰልጣኝነት የቆዩት እና በአሁኑ ሰአት ደደቢትን በድጋሚ ሲያሰለጥኑ የነበሩት አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ በድንገተኛ ህመም ከዚህ አለም በምት ተለይተዋል፡፡

በተጫዋችነት በምድር ጦር ረጅም አመታትን የተጫዋችነት ዘመንን ያሳለፉት አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ በአሰልጣኝነት ደግሞ መከላከያን በመያዝ ስራቸውን ጀምረዋል በኢትዮጵያ ባንኮች (ንግድ ባንክ) እና ደደቢት አሳልዋል በተለይ ደደቢትን ይ 2005 ክለቡን የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን በማድረግ አሰልጣኙም ኮከብ አሰልጣኝ ተብለውም በዛው አመት መመረጥም ችሏል ደደቢትን በመልቀቅም ወደ ወልዲያ በማምራት ወልዲያን ከታች ወደ ፕሪሚየር ሊግ አሳድገዋል በፕሪሚየር ሊጉም ወልዲያ በመያዝ ቆይታን በማድረግ ዳግም ወደ ደደቢት ተመልሰው በማሰልጠንም ላይ ነበሩ ፡፡

አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ በሊጉ ዳኞችን ያለ አግባብ ተናግረዋል በሚል ለሶስት ወራት ያህል ወራት ቅጣት ተጥሎባቸው ኢትዮጵያ ቡናን በገጠሙበት ጫወታ ክለቡም ከቅጣት መልስ መርተዋል ዛሬ በ25ተኛው ሳምንት ደደቢት ከአርባምንጭ ከተማ ጋር አሰልጣኙ ይመራሉ ተብሎ ቢታሰብም ትላንት ምሸት ላይ ከጎደኞቻቸው ጋር በመጫወት ላይ ሳሉ በገጠማቸው ከፍተኛ የጨጎራ ህመም ምክንያት ለህክምና ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል ተልከው የነበረ ቢሆንም ተጨማሪ ህክምና ስለሚያስፈልጋቸው ወደ ሀሌሉያ ሆስፒታል ቢወሰዱም ህይወታቸው በድንገት አልፏል
አሰልጣኝ ንጉሴ ባለትዳር እና የአንድ ልጅ አባት ናቸው።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ፉአድ ኢብራሂም (ኢትዮጵያ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ድንቅ የቅጣት ምቶች በነበሩት ጨዋታ ነገሌ ሲያሸንፍ ሀዋሳ በወልዋሎ ነጥብ ጥሏል

7 ጎሎች እና ሁለት ድንቅ የቅጣት ምት ጎሎች በነበሯቸው ሁለት ጨዋታዎች ነገሌ...