ዜናውን ለሰራው አካል ደውዬ ጠይቂያለው የተሳሳተ መረጃ ሰምቼ ነው ዜናውን የሰራሁት ይቅርታ ብሎኛል (አምጣቸው ኃይሌ የሀዋሳ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ)

👉👉ስራየን በሰላም በመስራት እያለሁ ሆን ተብሎ ሂይወቴን ለማበላሸት የተሰራብኝ ዜና ነው

👉👉ዜናውን ለሰራው አካል ደውዬ ጠይቂያለው የተሳሳተ መረጃ ሰምቼ ነው ዜናውን የሰራሁት ይቅርታ ብሎኛል

👉👉ክለቡ መረጃ ሳይሰጣቸው ለምን ዜናውን እንደሰሩት አላውቅም

👉👉ዱሬሳ ተጫዋቾች የጠየቋቸውን የተለያዩ ጥያቄዎች ክለቡ መልስ መመለስ ካልቻለ ክለቡን ተረከቡኝ የሚል ደብዳቤ ነው ያስገባው። (አምጣቸው ኃይሌ የሀዋሳ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ)

ትላንት የሀዋሳ ከተማው ረዳት አሰልጣኝ እና የቡድን መሪው ዱሬሳ ዱከሙ ሀዋሳ ከተማ ከስራቸው አሰናብቷቸዋል የሚል ዜና መውጣቱ የሚታወስ ሲሆን። ነገር ግን ዜናው ፍፁም የተሳሳተ ነው ሲሉ የክረቡ ረዳት አሰልጣኝ ከሚዲያችን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የሚከተለውን ብለውናል።

እርሶ ከሀዋሳ ተሰናብተዋል የሚል መረጃ በሚዲያ ተወርቷል እና ምንድነው ያለው ነገር

እኔ በማላውቀው ጉዳይ ከቡዱኑ ጋር ተለያይቷል የሚል መረጃ ወጥቷል። ዜናውን ለሰራው አካል ደውየ ጠይቂያለው የተሳሳተ መረጃ ሰምቼ ነው ዜናውን የሰራሁት ይቅርታ ብሎኛል። እኔም ይህ ይህ የተሳሳተ ዜና ሂወቴን ለማበላሸት ሆን ተብሎ የተደረገ ነው።

ክለቡ መረጃ ሳይሰጥ ዝም ተብሎ በአሉባልታ ወሬ ዜና መስራት በክለቡ ጫና አይፈጥርም

በጣም ጫና አለው እነሱም ክለቡ መረጃ ሳይሰጣቸው ለምን ዜናውን እንደሰሩት አላውቅም። ቀጥታ ደውየ ዜናውን ለፃፈው አካል ደውየለት ነበር ዜናውን አጥፍቼዋለ ይቅርታ ብሎኛል። ቢሆንም መረጃው ብዙ ሰው ጋር ደርሷል ከመቶ ሰው በላይ ነው የደወለልኝ ምን ተፈጠረ ብሎ። በክለቡ ውስጥ ምንም ሳይፈጠር ከተጫዋቾች ጋር አለመስማማታቸውን ተከትሎ ተሰናብተዋል የሚለው መረጃ ሆን ተብሎ የተደረገ ነው።

በአንተ እና ዱሬሳ መሀከል ከክለቡ ጋር ተያይዞ ያለው እውነታ ምንድነው

ዱሬሳ ተጫዋቾች የጠየቋቸውን የተለያዩ ጥያቄዎች ክለቡ መልስ መመለስ ካልቻለ ክለቡን ተረከቡኝ የሚል ደብዳቤ ነው እንጂ ያስገባው። ለሱም ከክለቡ መልስ እየጠበቀ ነው የሚገኘው ከኔም ጋር በተያያዘ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም።

ያለህ ቅሬታ ምንድነው

እኔ ያለኝ ቅረታ በጣም ተሰምቶኛል ምክንያቱም ከተጫዋቾቼ ጋር ሳልጣላ ተጣልቷል የተባለ ሲሆን። ከተጫዋቾቼ ጋር ያለኝ ነገር ሰላም ነው። ስራየንም በመስራት እያለሁ ሆን ተብሎ ሂይወቴን ለማበላሸት የተሰራብኝ ዜና ነው።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor