መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ዘወትር ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃው ሳምንታዊዋና ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው ጠዋት እትሟ ምንም ነገር ይዛ ይሆን
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣብቸኛዋ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ

ዘወትር ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃው ሳምንታዊዋና ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው ጠዋት እትሟ ምንም ነገር ይዛ ይሆን

አጋራ
አጋራ

ዘወትር ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃው ሳምንታዊዋና ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው ሁሉ በነገው የጥር 29/2010 እትሟም የሚወዷቸውን የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ስፖርት ዘገባዎችን ለእናንተ ውድና የተከበራችሁ አንባቢዎቻችን ጠፋጭ በሆነ መልኩ በማቅረብ ልታስነብቦት የመጨረሻው ጫፍ ላይ ደርሳና ስራዋንም አጠናቅቃ ወደ ማተሚያ ቤት አምርታለች፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው እትሟ ከሀገር ውስጥ ይዛላችሁ ከምትቀርበው ዘገባ መካከል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የሆነው ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምርጫን አስመልክቶ ‘‘ለውዝግቡ መነሻ የሆኑ ግለሰቦች ለኢትዮጵያ ሲሉ ከምርጫው ወጥተናል ቢሉ ይከበራሉ እንጂ አይዋረዱም”” ሲል ለተጠየቀው ጥያቄ ምላሹን ሰጥቷል፤ ሻለቃ ኃይሌ ሌላ አክሎ ከሰጠው አስተያየት ውስጥም ‘‘አሁን ያለው እግር ኳስ ጦር ያማዝዛል ብዬ አላምንም” ሲልም ይናገራል፤ ሌላው ከሀትሪክ የነገ ዘገባ መካከል ኢትዮጵያ ቡናና ፋሲል ከተማ ካደረጉት ጨዋታ በኋላ የዕለቱን ዳኛ ለሽንፈታቸው ተጠያቂ ያደረጉት የፋሲል ከተማው አሰልጣኝ ምንተስኖት ጌጡ ‘‘ፋሲል ባልረባ ውሳኔ ተሸንፎ የሚፈረካከስ ቡድን አይደለም፤ ካሉ በኋላ እኔም ብሆን ጫና ውስጥ አይደለውም የስንብት ስጋትም የለብኝም” በሚልም ለተጠየቁት ጥያቄ የሰጡትን ምላሽ ከሀትሪክ የምታገኙ ይሆናል፡፡
የሀትሪክ ስፖርት ሌላው ዘገባ ውስጥ በየሳምንቱ በምናቀርበው የቀድሞ ተጨዋቾችን በምናስታውስበት የኦልዲስ በት ጉዲስ ዓምዳችን ላይ በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመኑ ለአየር ኃይል፣ ለኢትዮጵያ ወጣትና የዋናው ብሄራዊ ቡድን ውስጥ ተጫውቶ ያሳለፈውና በአሁን ሰዓትም ኑሮውን በሆላንድ ያደረገው ተደናቂው የቀድሞ ተጨዋች ገነነ መክብብንም እንግዳ አድርገን ያዋራነው ሲሆን ይህም ተጨዋች ለሀገሩ የእግር ኳስ እድገት አንድ ነገርን ሰርቶ ለማለፍ በመፈለግ አስተያየቶችን ሊሰጥና ስለ አጠቃላይ የእግር ኳስ ሕይወቱም የሚለን ይኖራል፡፡ ገነነ መክብብ በተጨዋችነት ዘመኑ ብዙዎች ያደንቁት የነበረ ሲሆን ይህም ተጨዋች ወደ ሀገሩ በመጣበት ወቅትም ‘‘በእግር ኳስ ያገኘሁትን አኩሪ ስም ብቻ ይዤ ከምቀመጥ ለሀገሬ እግር ኳስ እድገት የታዳጊ ወጣቶች አካዳሚ ለመክፈት ተዘጋጅቻለው ሲልም ምላሹን ሰጥቷል፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው የባህር ማዶ ሰፊ ዘገባዎቿ መካከል ማንቸስተር ዩናይትድ ኸርድስፊልድን ድል ባደረገበት ጨዋታ የቡድኑ አሰልጣኝ ጆሴ ሞውሪኒሆ ድሉ እንደሚገባቸው የተናገሩ ሲሆን አርሰናልን በተመለከተም ለቡድኑ ሰሞኑን ፊርማውን ያኖረው ኦባሚያንግ የመጀመሪያ የሆነውን ቃለ-ምልልስ የሰጠበት ዘገባም ቀርቧል፤ የአርሰናሉ አዲስ ፈራሚ ከተናገረው ውስጥ ‘‘ለአርሰናል በመፈረሜ ደስታዬ ከፍተኛ ነው” ሲል ከክለቡ ጋር ተያይዞም አሮን ራምሴ ስለነገሰበት የቅዳሜ ምሽቱም ጨዋታ የሚወዱት ዘገባ ቀርቦሎታል፤ ሌላው ሀትሪክ ልታስኮመኩሞት ከተዘጋጀችበት መረጃዎች መካከል ብራዚላዊው ዝነኛ ተጨዋች ዳንኤል አልቬስ ኔይማርን አስመልክቶ በሰጠው አስተያየት፤ ‘‘ኔይማር ትክክል ነው፤ ከሜሲ ጥላ ስር መውጣት ነበረበት‘‘ በማለት የሰጠው ዘገባም ቀርቧል፤ ሀትሪክ ስፖርት ከእነዚህ ዘገባዎች በተጨማሪ ሌሎችንም ጣፋጭ የሆኑ መረጃዎችን ይዛላችሁ የቀረበች ሲሆን የነገ እትሟ አያምልጦት፤ ሌሎችም ያልተሰሙ አዳዲስና ትኩስ ዘገባዎችንም በማለዳው እጅዎ ትገባለች፡፡
በርካታ አንባቢዎቻችን ባቀረባችሁልን ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት ሀትሪክን በሳምንት ሁለት ቀን በቅርቡ ይዘን እንቀርባለንና ጠብቁን፡፡ ተጨማሪና ትኩስ መረጃዎችን በርካታ ተከታታዮች ባሉት hatricksport.com ድረ-ገፃችን ይጎብኙን፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
መልካም ንባብ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...