በፖናማ እና ኮስታሪካ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የሴቶች ከ20 አመት በታች አለም ዋንጫ ለመካፈል በአሰልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል የሚመራው የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በአለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የቡሩንዲ አቻውን ከሜዳ ውጭ 5-0 ካሸነፈ በኋላ ስለ ጨዋታው እና ስለብሄራዊ ቡድኑ የሚከተለውን ብለዋል።

ስለጨዋታው
- ማሰታውቂያ -
“በውጤቱ በጣም ደስተኛ ነኝ የኢትዮጵያ ህዝብንም እንኳን ደስ ያላቹህ ማለትን እወዳለሁ ውጤቱ ካሉኝ ተጫዋቾቼ ጋር በነበረን ጊዜ በተግባር እና በንድፍ ሀሳብ ትምህርት ታግዞ የመጣ ነው።”
“የተጫዋቾችም አቀባበል ድንቅ ነበር። በእግር ኳስ ውጤት እንዲመጣ ከተፈለገ ከመፈራራት ይልቅ መከባበርን ትልቁ ድርሻ ይወስዳል።”

“ይህ ውጤት ጅማሪያችን እንጂ ፍፃሚያችን አያሳይም በቀጣይም በርካታ ስራዎችን መስራት ይጠበቅብናል። ክፍተቶቻችን በማረም የተሻለ ስራ መስራት ይኖርብናል። በዚህ ውጤት ላይ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ተወክለው አብረውኝ ሲያግዙኝ የነበሩት እንዲሁም የሙያ አጋሮቼን ስለሁሉም ነገር ከልብ አመሰግናለሁ።”


