ዋልያዎቹ መስከረም 2 መቐለ ይገባሉ

 

በካሜሩን አዘጋጅነት ለሚካሄደው ቻን 2020 ማጣሪያ መስከረም 11 ሩዋንዳን ሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን መስከረም 2 ጨዋታው ወደ ሚካሄድበት መቐለ ሚጓዝ ይሆናል።

በመጀመርያ የማጣሪያ ጨዋታ የጁቡቲ አቻውን በደርሶ መልስ ማሸነፍ የቻለው የዋልያዎቹ ስብስብ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የሌሴቶ ብሄራዊ ቡድንን ከገጠመው ስብስብ ከኢትዮጵያ ውጪ ከሚጫወቱት ሽመልስ በቀለ፣ጋቶች ፖኖም፣ቢንያም በላይ፣ዑመድ ኡኩሪ ምትክ አዳዲስ ተጨዋቾች ሚጠራ ይሆናል።

ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን አንዲያስተናግድ ገደብ ያለው ፍቃድ በካፍ የተሰጠው ትግራይ ስታድየም በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጨዋታ ሚያስተናግድ ይሆናል።

Hatricksport website writer

Twitter