መነሻ ገጽ Transfer news ወልዋሎ ዓድግራት ዩኒቨርሲቲ ሁለት የውጭ ተጨዋቾችን ለሙከራ ሲያመጣ ከራያ አዘቦ ለአንድ ተጫዋች የሙከራ እድል ሰጥቷል::
Transfer newsወልዋሎዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

ወልዋሎ ዓድግራት ዩኒቨርሲቲ ሁለት የውጭ ተጨዋቾችን ለሙከራ ሲያመጣ ከራያ አዘቦ ለአንድ ተጫዋች የሙከራ እድል ሰጥቷል::

አጋራ
አጋራ

ባሳለፍነው ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪሜየርሊግ ከመውረድ ለጥቂት የተረፈው ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ2011 ኢትዮጵያ ፕሪመየር ሊግ ተፎካካሪ ለመሆን በክረምት የተጨዋቾች ዝውውር በንቃት እየተሳተፈ ይገኛል።

እስካሁን ድረስ ስድስት ተጨዋቾችን ያስፈርመው ኣሰልጣኝ ፀጋይ ኪዳነ ማርያም በአጥቂ ክፍል ያለውን ኣማራጭ ለማብዛት ሻሂድ ባቢንቶን ፋዩ ከናይጀርያ እንዲሁም ካራንጎን ከማሊ ለሙከራ ኣምጥቷል።ናይጀርያዊው ባቢንቶን ፋዩ በ2017 ዓለም ዋንጫን ያነሳው የናይጀርያ ከ17 ዓመት በታች ቡድን ውስጥ የነበረ ሲሆን በክለብ ደረጃም ለሱማል፣ፕራይም እና ኦል ስታርስ መጫወት ችሏል። ከሁለቱም ተጨዋቾች የተሳካ ጊዜ ሚያሳልፈው አንድ ተጨዋች በቋሚነት እሚፈርም ይሆናል።

በተጨማሪም አምና አንደኛ ሊግ ላይ ከራያ አዘቦ ጋር ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው ሰመረ ካሕሳይ ከዋና ቡድኑ ጋር እየተዘጋጀ ይገኛል።ግብ ጠባቂ በማፈላለግ ላይ ሚገኙት ወልዋሎ አዲግራቶች በቅርብ ቀን የውጭ ዜጋ ግብ ጠባቂ እንደሚያስፈርሙ ይጠበቃል።

ሰመረ ካሕሳይ
ሰመረ ካሕሳይ

መቐለ ላይ ቅድመ ውድድር(pre season) ዝግጅታቸውን በማድረግ ላይ ሚገኙት ወልዋሎ ዓ/ዩኒቨርሲቲ በትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ሽቶ ሚድያ ትብብርነት በሚዘጋጀው ሲቲ ካፕ እንደሚሳተፋም ታውቋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...