መነሻ ገጽ ሪፖርት ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲና ድሬዳዋ ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል
ሪፖርትወልዋሎየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግድሬዳዋ ከተማ

ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲና ድሬዳዋ ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል

አጋራ
አጋራ

በትግራይ ኢንተርናሽናል ስታድየም የተካሄደው የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲና ድሬዳዋ ከተማ ጨዋታ ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።ሁለቱም ቡድኖች በእምስተኛው ሳምንት ተጋጣሚያቸውን ድል አድርገው በጥሩ የማሸነፍ ስነ-ልቦና ወደ ጨዋታው እንደመምጣታቸው ጥሩ ጨዋታ ይታይበታል ተብሎ ቢጠበቅም፤ይህ ሚባል ተመልካችን ሚስብ ጨዋታ ሳይታይበት ጨዋታው ያለ ግብ አቻ ተጠናቋል።

መከላከያን ከገጠመው ቡድን ዋለልኝ ገብሬን በእማኑኤል ጎበና ቀይረው ወደ ሜዳ የገቡት ወልዋሎዎች የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ቢወስዱም በጨዋታው መጀመርያ ኤፍሬም እሻሞ ሞክሮት ሳምሶን እሰፋ ካዳነበት ኳስ ውጪ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ማድረግ እልቻሉም።

በዮሐንስ ሳህሌ እሚመሩት ድሬዳዋ ከተማ ደደቢትን ካሸነፈው ቡድን ራምኬልን በወሰኑ ማዜ ቀይረዋል።በ4-4-2 የጨዋታ ስልት ሲከላከሉ አራት ተከላካዮችና አማካዮችን በመጠቀም ሁለት ሳጥኖችን በመስራት የወልዋሎ እጥቂዎችና እማካዮችን የመጫወቻ ቦታ እንዳያገኙ በማድረግ የወልዋሎ የማጥቃት እንቅስቃሴን ሲያጨናግፋ ታይቷል።ፊት ላይ በተሰለፋት ኢታሙና ኬይሙኒና ሳላ እብዱላሂ ላይ ትኩረት ያደረገው የድሬዳዋ የማጥቃት እንቅስቃሴ አልፎ አልፎ የግብ እድሎችን ሲፈጥሩ ነበር።

ከመጀመርያው እጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ የታየበት ሁለተኛው እጋማሽ በሁለቱም ቡድኖች በኩል ለግብ የቀረቡ አስደንጋጭ ሙከራዎችን ኣስተናግዷል።ባለሜዳዎቹ ወልዋሎዎች አብዱራህማን ፋሱይኒን በፕሪንስ ሰርቪንሆ ቀይረው በመግባት ከሁለቱ መስመር በሚነሱ ኳሶች የግብ እድሎችን መፍጠር ችለዋል፤በ79ኛው ደቂቃ አማኑኤል ጎበና ብረት የመለሰበት እንዲሁም የግቡ ቋሚ ብረት የመለሰበት በተጨማሪም የፕሪንስ እና የብርሃኑ ቦጋለ ሙከራዎች ተጠቃሽ ናቸው።ድሬዎችም ከመጀመርያው አጋማሽ ቡድን ሥስት ቅያሬዎችን በማድረግ በመልሶ ማጥቃት ጥሩ ሚባሉ የግብ እድሎችን ፈጥረዋል፤ሲላ እብዱላሂ ከቅጣት ምት ኢታሙና ኬይሙኒ ከማእዘን ምት ያገኙዋቸው የግብ እድሎች ተጠቃሽ ናቸው።

ስድስት ቢጫ ካርዶችን ያስተናገደው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ግብ ሳያስተናገድ በእቻ ዉጤት ተጠናቋል።


የ6ኛ ሳምንት መርሀ ግብር ጨዋታዎች ነገ ሲቀጥል 6ጨዋታዎች እሚደረጉ ይሆናል

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ወላይታ ድቻዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

“የቀዶ ጥገና ህክምና ይደረግለታል” የወላይታ ድቻ ስራ አስኪያጅ አቶ ምትኩ ሐይሌ

ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከባድ ጉዳትን ያስተናገደው ወጣቱ ተጫዋች ቅዱስ ቂርቆስ በምን...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...