ወልዋሎ ከጋናዊው አማካይ ጋር ተለያይተዋል

 

በክረምቱ የተጨዋቾች መስኮት ዝውውር ከዳርባንዲክሃን ወልዋሎን የተቀላቀለው ኬኔዲ አሽያ በጋራ ስምምነት ከክለቡ ጋር ተለያይትዋል።

አብዛኛዎቹን የመጀመርያ ዙር ጨዋታዎች ተጠባባቂ ላይ ያሳለፈው የቀድሞው የሲዳማ ቡና፣ኤሲ ትሪፖሊ፣አል ሂላል፣ኤስኪ ብራን፣ሊብያ ፕሮፌሽናልስ ተጨዋች ኬኔዲ አንድም ጨዋታ በቀዋሚነት ሳይጀምር ከቢጫ ለባሾቹ ጋር መሰናበቱ አስገራሚ ሆኗል።

አዲስ አሰልጣኝ በማፈላለግ ላይ ያሉት ወልዋሎዎች የውድድሩ አጋማሽ ዓመት የተጨዋቾች መስኮት ዝውውር ላይ በርካታ ተጨዋቾችን ያስፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Hatricksport website writer

Twitter

ዳዊት ብርሀነ

Hatricksport website writer