ወልዋሎ አዲግራት ዩ. ተጫዋች በይፋ አስፈርሟል !

 

ወልዋሎ አዲግራት በአዲሱ አሰልጣኛቸው እየተመሩ ዮናስ በርታን የግላቸው ማድረግ ችለዋል ::

ከቀናቶች በፊት አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደ ጊዮርጊስን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠሩት ወልዋሎዎች ብዛት ያላቸው አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ እየቀላቀለ ይገኛል ::

በዛሬው እለትም በዝውውር መስኮቱ ስሙ ከወላይታ ዲቻ ጋር በስፋት ሲያያዝ የቆየውን የቀድሞውን የባህርዳር ከተማ፣ደቡብ ፖሊስ አማካይ ዮናስ በርታ ከሳምንት በፊት ከአዳማ ከተማ በስምምነት ከክለቡ ጋር መለያየቱን ተከትሎ በይፋ ወደ ቡድን ስብስቡ መቀላቀል ችሏል ::

ዮናስ በርታ በወልዋሎ አዲግራት ቤት የሚያቆየውን የአንድ ዓመት ውል ተፈራርሟል ::

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor