በዮሴፍ ከፈለኝ
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ እስከ ሰኔ 30/2011 ድረስ ውል ያላቸውን ወግደረስ ታዬና መኩሪያ ደሱ በህገወጥ መንገድ ማሰናበቱ ተገቢ ባለመሆኑ ደመወዛቸውን ከፍሎ እንዲመልስ የተወሰነውን የዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ እንዲፈጽም ተወሰነበት።አሰልጣኙ ጸጋዬ ኪዳነማርያም ግን ሁለቱንም አልፈልግም በማለቱ በፌዴሬሽኑ ዋና ጸሐፊ ሰለሞን ገ/ስላሴ አደራዳሪነት የ6 ወር ደመወዝ ከፍሎ እንዲሰናበቱ ክፍያው በ10 ቀን ውስጥ ተግባራዊ እንዲደረግ ተስማሙ።
ክፍያው ሳይፈጸም 1 ወር በማለፉ ግን ፌዴሬሽኑ ከሰኞ ጀምሮ ውሳኔው ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ ማገዱን በቢሮው ቋንቋ ከጽ/ቤቱ ምንም አይነት ግልጋሎት እንዳያገኙ ወስኗል።
አታክልቲ ጸጋዬ ግን የ10 ወር ደመወዙን ተቀብሎ
በሰላም መለያየቱ ታውቋል።በሊጉ 2 ጨዋቴ አድርጎ ሁለቱንም ጎል ሳያስቆጥር የተሸነፈው ወልዋሎ በሁለቱም መስመር ውጤታማ አለመሆኑ አነጋጋሪ ሆኗል።

አስተያየት ይስጡ