ወልዋሎ ሰሞኑን ለተጫዋቾቹ ደሞዝ ሊከፍል ነው

ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ በዚህ ሳምንት ደሞዝ ለመክፈል የሚያስችለው የሰባት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አግንቷል።

ክለቡ ዛሬ ከከተማ አስተዳደሩ የሁለት ሚሊዮን ከአዲግራት ዩንቨርሲቲ ደግሞ የአምስት ሚሊዮን ብር በጠቅላላው ደግሞ የሰባት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማግኘቱ ነው ከሰሞኑ ለተጫዋቾቹ ደሞዛቸውን ለመክፈል የወሰነው። ፌደሬሽኑ እስከ ሐምሌ 5 ድረስ ሁሉም ክለቦች ደመዝ ከፍለው ሪፖርት እንዲያደርጉ ባወጣው ትእዛዝ መሰረት ወልዋሎዎችም ለተጫዋቾች ያልከፈሏቸውን ውዝፍ የበርካታ ወራት ደሞዝ ቀድመው ለመክፈል ያሰቡት።