ወልቂጤ ከነማ በዝውውር ነቅቶ እየተሳተፈ ይገኛል !

በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎን እያደረጉ የሚገኙት ወልቂጤ ከተማዎች አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ ከመቀላቀል ባለፈ የተጫዋቻቸውን ውል በማራዘሙ ቀጥለዋል ።

በአሁን ሰዓትም የሁለት ተጫዋቾቻቸውን ውል ሲያራዝሙ አንድ ተጫዋች ማስፈረማቸው ተገልጿል ።

አሳሪ አልማሀዲ ከደቂቃዎች በፊት በክትፎዎቹ ቤት ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ለመቆየት የተስማማ ተጫዋች ሆኗል ።

አሳሪ አልማሀዲ ክትፎዎቹን ከመቀላቀሉ አስቀድሞ በሙገር ሲሚንቶ ፤ ወልዋሎ አዲግረታት ዩኒቨርስቲ በመጫወት ማሳለፉ ይታወሳል ።

ከአሳሪ አል አህመዲ በተጨማሪ ክትፎዎቹ የግብ ጠባቂያቸውን ጆርጅ ደስታን ውል ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ማራዘማቸው ታውቋል ።

በዛሬው እለት ቡድኑን መቀላቀሉ የተገለፀው ረመዳን ናስር ሲሆን ክትፎዎቹን ከስሑል ሽረ መቀላቀሉን ሀትሪክ ስፖርት ለማወቅ ችላለች ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor