ወልቂጤ ከተማ ግብ ጠባቂ አስፈረመ !

 

ከብሔራዊ ሊግ ባደጉበት የውድድር ዓመት ጥሩ ግስጋሴን በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው እየተመሩ ማድረግ የቻሉት ክትፎዎቹ ግብ ጠባቂያቸውን ይድነቃቸው ኪዳኔ ለፋሲል ከነማ አሳልፈው መስጠታቸውን ተከትሎ ዮሐንስ በዛብህን በምትኩ ማስፈረማቸው ተገልጿል ።

ዮሐንስ በዛብህ ያለፈውን የውድድር ዓመት በብሔራዊ ሊግ እየተወዳደረ በሚገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሲያሳልፍ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ቡና ሀዋሳ ከተማ ተጫውቶ ማሳለፉ አይረሳም ።

ዮሐንስ በዛብህ ከዛሬው የፊርማ ስነ ስርዓት በኋላ ከሀትሪክ ስፖርት ጋር ቆይታን ሲያደርግ ” ለኢትዮ ኤሌክትሪክ አመራሮች በተለይም ለክለቡ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ደንድርን ከልብ ላመሰግናቸው እወዳለሁ ። ከብሔራዊ ሊግ ወደ ሊጉ በመመለስ ዳግም በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ በወልቂጤ ከተማ መለያ መጫወት በመቻሌ ደስተኛ ነኝ ” ሲል አስተያየቱን ለሀትሪክ ስፖርት ተናግሯል ።

ወልቂጤ ከተማ ሊጉ በኮሮና ቫይረስ እሰከ ተቋረጠበት ድረስ በ 22 ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዘው ይገኙ ነበር ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor