መነሻ ገጽ ሪፖርት ወላይታ ድቻና ጅማ አባ ጅፋር ያለምንም ግብ አቻ ተለያዩ።
ሪፖርትወላይታ ድቻየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግጅማ አባጅፋር

ወላይታ ድቻና ጅማ አባ ጅፋር ያለምንም ግብ አቻ ተለያዩ።

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 29 ሳምንት ጨዋታ የወራጅ ቀጠና ላይ ያለው ወላይታ ድቻ ዋንጫ ለማንሳት ከሚፎካከረው ጅማ አባጅፋር ጋር ነጥብ ተጋርቷል።

መጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በባለሜዳዎቹ ፈጣን የጨዋታ እንቅስቃሴና ጎል ለመሆን የሚችሉ ሙከራዎችን በማድረግ ተጋጣሚውን ለማስጨነቅ ሞክሩዋል፡፡

በተላይ በ22ኛው ደቂቃ ላይ ጃኮ አራፋት የሞከረውና የግቡ አግዳሚ የመለሰው አጋጣሚ ተመልካቹን ቁጭት ውስጥ የከተተች ነበር፡፡

የወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም በከባድ ዝናብ ሜዳው ውሀ በመቋጠሩ ተጫዋቾች ኳስን በተገቢው መንገድ እንዳያንቀሳቅሱ አድርጓቸው እንደነበር ተስተውሏል ።

ይሁን እንጂ ለሁለቱም ቡድኖች ነጥብ ማስመዝገብ አስፈላጊ ስለሆነባቸው ጨዋታቸውን ከባድ ውጥረትና ጉሽሚያ የታጀበበት አድረጎታል ።

ጅማ አባ ጅፋር በበኩሉ በመከላከልና በመልሶ ማጥቃት የጨዋታ እንቅስቃሴ ጨዋታውን ሲቆጣጠር አምሽቷል፡፡

በርካታ ደጋፊዎች በሜዳው ተገኝቶ ስፖርታዊ ጨዋነት በተላበሰ መልኩ ቡድናቸውን አበረታትተዋል፡፡

በተለይም የጅማ አባ ጅፋር ቡድን ደጋፊዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድን ለመደገፍ ሰኔ 16 መስቀል አደባባይ ላይ ህይወቱን ያጣውን የወላይታ ተወላጅ የዮሴፍ አያሌውን ፎቶ መያዛቸው ጨዋታው የተለየ ድባብ እንዲኖረውና በሜዳው የአንድነት ዜማ እንዲሰማ አድርጎት ነበር፡፡

የአሰልጣኞች አስተያየት

አሰልጣኝ ዘነበ ፍስሃ – ወላይታ ድቻ

ቡድናቸው ያደረገው ተጋድሎ የሚያስደስት መሆኑን ገልጸው ጎል የማግባት ችግሮች ቡድኑን ዋጋ እያስከፈለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ቀጣይ ጨዋታ በማሸነፍ በሊጉ ለመቆየት ተስፋ አለን።

አሰልጣኝ ገብረመድህን ሃይሌ – ጅማ አባጅፋር

በተገቢዉ ኳስ ይዘን ለመጫወት ሜዳው ዕድል አልሰጠንም።
ሆኖም ያገኘነው 1 ነጥብ አላስከፋንም። በቀጣይ። በሜዳቸን ያለንን ጨዋታ በማሸነፍ ዋንጫውን እናነሳለን፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሽንፈት ሲገጥመው በድንጉዛ ደርቢ የጦና ንቦቹ እና ኤሌክትሪክ ድል ቀንቷቸዋል

በሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሽንፈትን በሸገር ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የ30ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች መናፍ ዐወል (አዳማ ከተማ): ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...