መነሻ ገጽ አፍሪካ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ | ወርቃማ አዲስ ታሪክ የፃፈው ወላይታ ድቻ ከውድድር ውጭ ሁኗል
አፍሪካኮንፌድሬሽን ካፕዜናዎች

ኮንፌደሬሽን ዋንጫ | ወርቃማ አዲስ ታሪክ የፃፈው ወላይታ ድቻ ከውድድር ውጭ ሁኗል

አጋራ
አጋራ

ኢትዬጵያን በመወከል በአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ በመሳተፍ ላይ የነበረው ወላይታ ድቻ በታንዛኒያው ያንግ አፍሪካንስ ተሸንፎ ከውድድሩ ውጭ ሁኗል፡፡

በአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ወደ ምድብ ድልድል ለመግባት የታንዛኒያውን ያንግ አፍሪካንስ በሜዳው ያስተናገደው ወላይታ ድቻ 1-0 ቢያሸንፍም፡በደርሶ መልስ ድምር ውጤት በያንጋ 2-1ተሸንፎ ከውድድሩ ወጥቷል፡፡

በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዬጵያን በመወከል በአፍሪካ መድረክ፡ በአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ሲሳተፍ የነበረው ወላይታ ድቻ ፡በክለቡ ታሪክ አዲስ ወርቃማ ታሪክ አፅፎ ፡ወደ ምድብ ድልድል ለመግባት የነበራቸው ህልም ሳይቋጭ በታንዛኒያው ያንጋ ተሸንፈው ከውድድሩ ውጭ ሁኗል፡፡

ወላይታ ድቻ በተሳትፎ ቆይታው በቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የዛንዚባሩን ዚማሞቶ በደርሶ መልስ ውጤት 2-1 በመርታት ወደ ቀጣዩ ማጣሪያ ሲያልፉ ያገኙት የአፍሪካውን ስመ ገናና የግብፁን ዛማሌክ ነበር፡፡የጦና ንቦቹ የ5ጊዜ የአፍሪካ ቻምፒዬንስ ሊግ አሸናፊውን ዛማሌክ በሜዳቸው 2-1 በማሸነፍ በመልሱ ጨዋታ ግብፅ ላይ 2-1 ቢሸነፉም በድምር ውጤት 3 እኩል በመሆናቸው በተሰጠው የመለያ ምት ንቦቹ ዛማሌክን 4ለ3 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ሲያልፉ የታላላቅ መገናኛ ብዙሃንን ትኩረትን መሳባቸው ይታወቃል፡፡

ወላይታ ድቻዎች በሚሳተፉበት የአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ካኘ ወደ ምድብ ድልድል ለመግባት የታንዛኒያውን ያንግ አፍሪካንስ ማሸነፍ ይጠበቅባቸው ነበር፡፡በመሆኑም ድቻዎች በመጀመሪያው ጨዋታ ወደ ታንዛኒያ ዳሬሰላም አቅንው ያንጋን በገጠሙበት ጨዋታ በባለሜዳዎቹ 2-0 ተሸንፈው ሲመለሱ በመልሱ በሜዳቸው ጨዋታ ውጤቱን ቀልብሰው ወደ ምድብ ድልድል ለማለፍ አስቸጋሪ እንደሚሆንባቸው ተጠብቆ ነበር፡፡

ድቻዎች ዛሬ በሜዳቸው በሀዋሳ አለም አቅፍ ስታዲዬም ያንጋን በገጠሙበት ጨዋታ ገና በጨዋታው መጀመሪያ 2ኛው ደቂቃ ላይ በጃኮ አረፋት አማካኝነት ግብ በማስቆጠር መሪ በመሆን ተጋጣሚያቸው ላይ ጫና ማሳደር ቢችሉም በአጠቃላይ በጨዋታው የ90 ደቂቃ እንቅስቃሴ ያገኟቸውን የግብ አጋጣሚዎች በአግባቡ ሳይጠቀሙባቸው ተጋጣሚያቸውን ያንግ አፍሪካንስ 1-0 ቢረቱም በደርሶ መልስ ድምር ውጤት 2-1 ተሸነፈው ከውድድሩ ሲወጡ ፡ድቻዎች፡ዳሬሰላም ላይ ያስተናገዷቸው 2 ግቦች የማለፍ ህልማቸውን ያጨለሙ ሁነው ተመዝግበዋል፡፡

የጦና ንቦቹ በአፍሪካ መድረክ በነበራቸው ቆይታ ከኮኮቦቻቸው መካከል ፡በዛብህ መለዬ፡ጃኮ አረፋትና፡ሀይማኖት ወርቁ፡የግብፅ ክለቦች አይን ማረፊያ የነበሩ ሲሆን፡3ቱ ተጨዋቾች የኢትዮጵያ ኘሪሚዬር ሊግ ሲጠናቀቅ ለሙከራ ወደ ተለያዩ የግብፅ ክለቦች እንደሚያመሩ ይጠበቃል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ፉአድ ኢብራሂም (ኢትዮጵያ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...