ክለቦች የተጨዋቾቻቸውን ደመወዝ እየከፈሉ ነው

👉ኢትዮጲያ ቡና ሰባተኛው ክለብ ሆነ

👉ክለቦች የተጨዋቾቻቸውን ደመወዝ እየከፈሉ ነው

በተጨዋቾችና ክለቦች መሃል የደመወዝ ክፍያ ጉዳይ
ሲያወዛግብ ቆይቷል፡፡ ከ2 እስከ 5 ወር ደመወዝ ያልተከፈላቸው ተጨዋቾችና ክለቦቻቸው መሃል የነበረውም አለመግባባት በተጨዋቾች ማህበርና በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው መሃልም ሌላ ውዝግብ ፈጥሮ ከሰሞኑ ሲያወዛግብ ቆይቷል፡፡ አሰልጣኙ ክለቦችና መንግስት ብር ከሌላቸው ምን ያድርጉ ሰው እያለቀ ደመወዝ መጠየቅ ተገቢ አይደለም ቢሉም ኢትዮጲያ ቡና ከተጨዋቾቹ ጋር ያለውን የደመወዝ ጥያቄ በመመለስ 7ኛው ክለብ ሆኗል…ከ16ቱ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች 9.ክለቦች ከተጨዋቾች ጋር ያላቸው የደመወዝ ክፍያ ውዝግብ አሁንም አልቆመም…የኢትዮጲያ ፕሮፌሽናል ተጨዋቾችና ባለሙያዎች ማህበር ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ ኢትዮጲያ ቡናን ጨምሮ የከፍተኛ ሊግ ክለቦች የሆኑት መከላከያ..አዲስ አበባ ከተማና ኢኮስኮ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ክለብ የሆነው የንግድ ባንክ ሴቶች ቡድን ከተጨዋቾቻቸው ጋር የገጠሙትን የደመወዝ ክፈሉ ውዝግብን በሰላም በማጠናቀቃቸው አመስግኗል።


Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport