ፕሪምየር ሊጉ ገና ዘጠነኛ ሳምንታ ላይ ደርሷል ሆኖም ግን የፕሪምየር ሊጉ ክለቦች ለተጫዋቾቻቸው እና አሰልጣኞች ማስጠንቀቂያ መስጠትን ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል። ዛሬ ደግሞ ድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኙን ጨምሮ ለአምስት ተጫዋቾች ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ክለቡ በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ ገልጷል።
የክለቡ መረጃ እንደሚከተለው ነው
ቡርቱካናማዎቹ አሰልጣኝ ስምኦን ዓባይን እና ናይጀሪያዊው አጥቂ ባጅዋ አደግሰንን ጨምሮ ሌሎች አምስት ተጫዋቾች ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። አሰልጣኙ ስምኦን ዓባይ ቡድኑ በስምንተኛው ሳምንት አዲስ አበባ ስታዲዮም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያደረገው ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ በጥቂት የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ያልተገባ በደል ቢደርስባቸውሞ ክለቡ የሚታወቅበት እና መልካም ስነምግባር ወደ ጎን በመተው አራት ተጫዋቾቹን እና አንድ አሰልጣኝ ሁኔታዎችን በጨዋነትና በመልካም ስነምግባር ማረጋጋት ነበረባቸው በማለት በቃል ደረጃ አስጠንቅቋል። አጥቂው ባጅዋ አደግሰን ደግሞ ወደ ቡድኑ ከመጣ ጀምሮ የሚጠበቅበትን ግልጋሎት እየሰጣ አለመሆኑ ተከትሎ ከአስራ አምስት ቀን በፊት አቋሙን እንዲያስተካክል ቢነገረውም ማስተካከል ባለመቻሉ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ደርሶታል።
አስተያየት ይስጡ