ካፍ የውድድር ቀኖችን ይፋ አደረገ !

 

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከተቋረጠ ውድድሮች መካከል የክለቦች የውስጥ ውድድር ሲሆን ካፍ ከሰዓታት በፊት የካፍ ሻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫዎች የመካሄጃ ቀናት ይፋ አድርጓል ።

ይህንንም ተከትሎ የግማሽ ፍፃሜ የኮንፌዴሬሽን ካፕ ጨዋታዎች ከመጪው መስከረም 12 ጀምሮ እንደሚካሄድ ይፋ ሆኗል ።

በዚህም መሰረት :-

1. ፒራሚድ ክለብ ( ግብፅ ) ከ ሆሮያ ክለብ ( ጊኒ )

2. ቤርካን ክለብ ( ሞሮኮ ) ከ ሁሳ ( ሞሮኮ ) ጨዋታቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል ።

የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታዎች ከአምስት ቀናት በኋላ መስከረም 17 የሚደረግ ይሆናል ።

በሌላኛው የውድድር መድረክ በጉጉት በሚጠበቀው የሻምፒየንስ ሊግ መርሀ ግብሮች ቀሪ ጨዋታዎች በሞሮኮ እና ግብፅ ላይ በደርሶ መልስ እንደሚካሄዱ ሲገለፅ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች መስከረም 15 እና 16 ሲካሄዱ የመልስ ጨዋታዎች በሳምንቱ መስከረም 22 እና 23 እንደሚካሄዱ ካፍ ይፋ አድርጓል ።

ካፍ በላከው ደብዳቤ እንዳሳወቀው ሁሉም ጨዋታዎች በዝግ እንደሚካሄድ በይፋ አሳውቋል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor