ካፍ የውድድር ቀኖችን ይፋ አደረገ !

 

ካፍ የቀጣይ የውድድር ዓመት የአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ጨዋታዎች የሚካሄዱበትን ቀን ይፋ አድርጓል ።

በዚህም መሰረት :-

የቅድመ ማጣርያ ጨዋታዎች የመጀመሪያ ዙር ከ ህዳር 11 – 13 ሲካሄዱ የመልስ ጨዋታዎች ከ ህዳር 18 እስከ 20 እንደሚካሄዱ ይፋ ሆኗል ።

ይህንን ተከትሎ የመጀመሪያው ዙር የማጣርያ ጨዋታዎች ከታህሳስ 2 -4 ሲካሄዱ የመልስ ጨዋታዎች ከ ታህሳስ 9 – 11 ይካሄዳሉ ።

ከእነዚህ የማጣርያ ጨዋታዎች በመቀጠል ወደ ምድብ ድልድሉ የሚገቡ ቡድኖች ከ የካቲት አምስት ጀምሮ ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ ።

ከዚህ በተጨማሪ ካፍ በዛሬው እለት አስራ ሁለት ሀገራት ( አልጄርያ ፣ አንጎላ ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ፣ ግብፅ ፣ ጊኒ ፣ ሊቢያ ፣ ሞሮኮ ፣ ናይጄርያ ፣ ደቡብ አፍሪካ ፣ ሱዳን ፣ ቱኒዚያ እንዲሁም ዛምቢያ ) እያንዳንዳቸው በውድድር መድረኮቹ ላይ በሁለት ክለቦች እንደሚወከሉ ይፋ አድርጓል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor