ካሜሮናዊው ታዳጊ ስቴቭ ሙቮ ክብረ ወሰን ሊሰብር ተዘጋጅቷል

 

ከጥቂት አመታት በፊት የአፍሪካ ተጨዋቾች ወደ አውሮፓ በስደት መልክ በመሄድ በተለያዩ ትናንሽ ክልቦች በርካታ ሙከራዎችን በማድረግ ነበር የአውሮፓ እግርኳስ ሂይወታቸውን የሚጀምሩት። አሁን አሁን ላይ ግን የአፍሪካ ሊጎች መጠንከር እና የእግርኳስ ተጨዋቾች ወኪሎች በመላው አለም መንሰራፋት ታክሎበት አፍሪካውያን ኮከቦች በቀጥታ የአውሮፓ እና ሌሎች የተለያዩ አሁጉራት ሊጎችን ሲቀላቅሉ ማየት ችለናል።

ከወደ ካሜሮን በተሰሙ ወሬዎች መሰረት ታዳጊው ካሜሮናዊ ተስፈኛ ስቴቭ ሞር ከካሜሮኑ አዙር ስታርስ አካዳሚ በፈረንሳይ ሊግ አንድ ለሚጫወተው ቱሉዝ ለመፈረም ከጫፍ ደርሷ። የፈርንሳዩ ክለብ ለተጨዋቹ ዝውውር 1ሚሊዮን ይሮ የሚከፍል ሲሆን ይሄም በካሜሩን የዝውውር ታሪክ ውዱ ወደ አውሮፓ የሄደ ተጨዋች ያደርገዋል።

ሙቮ በ2019ኙ የካፍ ከ19 አመት ጨዋታ ኮከብ ተጨዋች ተብሎ የተመረጠ ሲሆን በውድድሩም ሀገሩን የዋንጫው ባለቤት ማድረግ ችሏል። የተጨዋቹ ወኪል የሆነው ኡቶፒያ ግሩፕ የተባለው ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ የሳሙኤል ኤቶ እና የቀድሞው የካሜሮን ግብ ጠባቂ ፋብሪክ ኦንዷ ወኪል እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።